ነገረ ሥላሴን በበዓል ለመመስከር እና የቸርነቱ፣ የምህረቱ ተካፋይ ለመሆን በዓለ ንግሥም ይከናወናል፡፡ በይበልጥም ሐምሌ 7 ቀን ለአብርሃም በድንኳን ደጃፍ መገለጡን እና ጥር 7 በባቢሎን በሰናዖር የተፈጸመውን ተአምር በማሰብ እናከብራለን፡፡ ዘፍ.18 ዘፍ.11.1-9

በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍት እንደተመዘገበው ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡ በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ› ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡ አለቃቸው ናምሩድ ይባላል ‹‹ ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እነርሱን ወግተን ሞትን እናርቅ ›› አላቸው ከዚያም ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣን ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹ አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው ….›› ይሉ ጀመር ቅድስት ሥላሴ ምንም እንኳ ምህረታቸው የበዛ ቢሆንም በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለሠለጠነባቸው እና ለሌሎች ከሀድያን ትምህርት ይሆን ዘንድ ‹‹ንዑ ንረድ ወንክዐው ነገሮሙ›› በማለት ቋንቋቸውን ለያዩባቸው የማይግባቡ፣ የማይደማመጡ…… ሆነው ተበታትነዋል፡፡ ባለማስተዋል የሠሩትንም ሕንፃ ዓመጻ ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ ይህን ያደረጉ ሥላሴ በመሆናቸው በዓሉ ጥር 7 ይከበራል፡፡
በአጠቃላይ ሥልጣን ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኑን እና በራስ ደካማ አመለካከት በመታበይ በሥላሴ ሥራ መግባት’ መጠራጠር ….. እንደሚጎዳ እንደዚሁም በጽኑ እምነት በመኖር እና በሥላሴ ስም የተጠመቅን ልጅነታችንን በኃጢአት ሳናሳድፍ በንስሐ ታጥበን እና በምግባር ጸንተን መጠበቅ እንደሚገባ የበዓሉ መልእክት ያስገነዝበናል፡፡ የታማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ እንደሚል ፡፡ ኤፌ. 4÷30
ሰላም ለአእዳዊክሙ እለ ፀሐፋ ኦሪተ
አመ ፆመ ሙሴ አርብዓ መዓልተ
ሥሉስ ቅዱስ ዘትለብሱ ስብሐተ
ከመ አዝነምክሙ በሰዶም እሳተ
በዲበ ፀርየ አዝንሙ መቅሰፍተ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
====🔅===🍁===🔅===🍁====
#ሼር #Share
👉 https://t.me/EMislene
👉 https://youtu.be/ARj1QE-ik38
====🔅===🍁===🔅===🍁====