ቤተ-ኤል

ነግህ በጊዜ ጸሎት አእዋፍ ሳይወነጭፍ ከማለዳ ሰማይ ፀሐይ ሳትነጥፍ ይሰማል አርጋኖን ከጉም ሽፋኗ ስር አቋቋም ዝማሬ ነፍስን የሚያሸብር ከሌሊት ወጋገን ከአናብርት ልቆ ከአርያም ብሔር መድረሻውን አውቆ የማኅሌት ክምር ኅሊና የሚሠውር እንደ መላእክቱ በምስጋና መስከር ይታየኛል ሕይወት ነፍስ የሚያለመልም ከጉልላቷ ስር…