✞✞✞ ጥቅምት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::…

ዘመነ ጽጌና የጌታ መሰደድ ምክንያት

(በዲ/ን ሕሊና በለጠ) በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለው ጊዜ ዘመነ ጽጌ/ ወርኃ ጽጌ ይባላል፡፡ የተዘሩ አዝርዕት በቅለው፣ የተተከሉ አትክልት ጸድቀው፣ አብበውና አፍርተው የሚታዩበት የጽጌ፣ የልምላሜ ጊዜ ነው፡፡ “አሠርጎኮ ለሰማይ በከዋክብት ወለምድርኒ በሥነ ጽጌያት ግብረ እደዊከ አዳም…

‹‹ አእምሮሽ የተመሰገነ ይሁን!››

ዘወትር ከአባታችን ሆይ ቀጥሎ በምናደርሰው ‹‹በሰላመ ገብርኤል›› በተሰኘው የጸሎት ክፍል ውስጥ ‹‹በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ›› የሚል የምስጋናና የምስክርነት ቃል ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ በመልክዓ ማርያም ውስጥም ‹‹ሰላም ለሕሊናኪ ሐልዮ ሠናያት ልማዱ ወገቢረ ምሕረት መፍቅዱ›› ማለትም ‹‹ምሕረት ማድረግ ለሚወድ መልካም…

ሥራህን ሥራ፤ ሌሎችን እርዳ፤ የሚጠቅም ሰውም ኹን! በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

  ሌሎች ሰዎችን ከማያድን ክርስቲያን በላይ የከፋ ምንም የለም፡፡ አንተ ሰው! ድኻ ነኝ የምትለኝ ለምንድን ነው? ኹለት ዲናር የጣለችዋ ሴት ትፋረድባሃለች፡፡ ከምናምንቴ ቤተ ሰብ እንደ ተወለድክ የምትነግረኝስ ለምንድን ነው? ሐዋርያትም ምናምንቴዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ታላላቅ መኾን ተችሏቸዋል፡፡ አለመማርህን ሰበብ አድርገህ…

መንፈሳዊ ዕድገት በቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት ውስጥ

አንድ አገልጋይ በመንፈሳዊ ሕይወቱ እየተጠቀመ መሆኑ የሚታወቀው የአገልግሎት ዘመኑ እየጨመረ ሲሄድ ትኅትናው እየጨመረ ከመጣ ነው፡፡ የአገልግሎት ብርታትና ጥንካሬ በዕውቀት መጨመር ወይም በታዋቂነት ብዛት ብቻ አይለካም፡፡ ብዙ ቦታዎችን በማዳረስና ብዙ ነገሮችንም በመሥራት ብቻ አይመዘንም፡፡ ከኢየሩሳሌም ያልወጣው ቅዱስ ያዕቆብ ነው ከሐዋርያት መካከል…

ብሒለ አበው

“በየጊዜው ለንስሐ መራኹ” (ቅዱስ እንጦንስ) “ፈሪሐ እግዚአብሔር ከሌለ ንስሐ የለም፡፡” “ቁጡ ብስጩ አትሁን ቁጣ ነፍስ ወደማጥፋት ይደርሳል፡፡” /ቅዱስ እንድርያስ/ “ቂም በቀል የሌለህ ሁን ቂም በቀል በሌላቸው ሰዎች መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉና” /ቅዱስ ታዴዎስ/ “ከኃይልና ከጩኸት ይልቅ ይቅርታና ትህትና ጠንካራ ናቸው፡፡” “ኃጢአት…

መንፈሳዊ አባባሎች

“የወጡ ማጣፈጫ ቅቤ ነው፡፡ የሃይማኖት ማጣፈጫ ግን ምግባር ነው፡፡” “ክርስትና እያዘኑ የሚደሰቱበት ሃይማኖት ነው”፡፡ “ለአጢያት ንስሐ መግባት ሕይወት ነው፤ አለመግባት ግን ሞት ነው”፡፡ “መንፈሳዊ መካሪ ርካሽ ሳይሆን ውድ ነው”፡፡ “መጽሐፍ ቅዱስ ምግብ ነውና ይመገቡት”:: “መጽሐፍ ቅዱስ ያብሩት ብርሃን ነውና”፡፡ “ለጠቢብ…

ይህን ያውቁ ኖሯል

የቅዱስ መርቆርዮስ ፈረስ ጌታው ከሞተ በኋላ 7 ዓመት በጌታው ተተክቶ አስተምህሮ በጥር 25 ቀን ተገደለ፡፡ የገላውድዮስ ፈረስ ከአፉ እሳት እየወጣ አሳውያኖችን ያቃትላቸው ነበር፡፡ የአቡነ አካለ ክርስቶስ መቋሚያ ቤተመቅደስ ሳይታጥን የቀረ እንደሆነ መቋሚያዋ ካለችበት ትሰወራለች፡፡ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገዳም በቅሎዎች ተጭነው…