አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

በየዓመቱ መጋቢት 5 የምናከብረው በዓል አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያረፉበት በዓል ነው፡፡ በዚኽ ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴዋም በትምህርቷም ኹሉ እኒኽን ታላቅና ቅዱስ አባት ታነሣለች፤ ታወድሳለች፤ ተጋድሎአቸውንም ለልጆቿ ታስተምራለች፡፡ ሀገራቸው ንሒሳ (ግብጽ) ሲኾን አባታቸው ስምዖን እናታቸውም አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ልጅ…

ታላቁ አባት አባ አቡነ ሙሴ ጸሊም

አቡነ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ተጋድሎአቸውን የፈጸሙት ግን በግብፅ ነው፡፡ መጀመሪያ ላይ እንደ አብርሃም በየዋህ ልቡና ሆነው ስነ ፍጥረትን በመመራመር እግዚአብሔር አምላካቸውን ያገኙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ወላጆቻቸው ፀሐይ ያመልኩ ስለነበር ከልጅነታቸው ጀምሮ ኃጢአት በሠሩ ቁጥር ‹‹ተው አምላካችን ፀሐይ ይጣላሃል›› ይሏቸው…

ሆሣዕና (ለሕፃናት)

በቤካ ፋንታ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም በኢየሩሳሌም በምትገኝ በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ነው የምኖረው፡፡ ከተወለድኩ አምስት ዓመት ሞልቶኛል፡፡ በዕለተ ሰንበት በቤት ውስጥ እየተጫወትሁ፣ እናቴም በጓዳ ሥራ እየሠራች ሳለን በድንገት የብዙ ሰዎች የዕልልታ ድምፅ በሰፈሩ ውስጥ ሰማን፡፡ እናቴም በፍጥነት ከጓዳ…

ደቂቀ ሰይጣን

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ (14261460ዓ ም) በዘመናቸው አምልኮ ጣዖትን አስቆማለሁ ብለው ቆርጠው ተነሥተው ነበር፡፡ ይህንን ነገር ለማስቆምም ሦስት ዓይነት መንገድ ለመጠቀም አሰቡ፡፡ መምህራንን እየላኩ ሕዝቡን ለማስተማር፣ ለማስተማርያ የሚሆኑ ድርሰቶችን እንዲዘጋጁ ለማድረግና ራሳቸውም ለማዘጋጀት፣ በመጨረሻ ደግሞ ከዚህ ሁሉ የተሻገረውን ለመቅጣት፡፡ በተለይም በአምልኮ…