ማንን ትፈልጋላችሁ ዛሬ በማለዳ

ጥያቄ ይዘን መጥተናል ዛሬ በማለዳ

ለመመለስ ዝግጁ ነን ዛሬ በማለዳ

እሁድ ምን ተፈጠረ?

ሰባቱ ሠማያት

መቶ ከነገደ መላዕክት

አራቱ ባሕርያት ጨለማና ብርሃን

ሰኞ ምን ተፈጠረ?

ውኃን ለሦስት ከፍሎ ሐኖስ ጠፈር ውቅያኖስ

ማክሰኞ ምን ተፈጠረ?

በእጅ የሚለቀሙ

በማጭድ የሚታጨዱ

በመጥረቢያ የሚፈለጡ

ረቡዕ ምን ተፈጠረ?

በቀንና በሌሊት የሚያበሩ

ፀሀይ ጨረቃና ከዋክብት

ሐሙስ ምን ተፈጠረ?

በባህር ውስጥ ሆነው በእግር የሚንሸራሸሩ

በልብ የሚሣቡ በክንፋቸው የሚበሩ

አርብ ምን ተፈጠረ?

በመሬት ላይ ሆነው በእግር የሚንሸራሸሩ

በልብ የሚሣቡ በክንፋቸው የሚበሩ እና ሰው

እግዚአብሔር አምላካችን 22ቱን ፍጥረታት እንዲህ ባለሁኔታ ፈጠራቸው

አምስቱ አዕማደ ምስጢራት

ስነ-ፍጥረት

የእመቤታችን ምስጋና

ማንን ትፈልጋላችሁ