“ሾለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደዳለን እንደሚታረዱ በጎችም ተቆጠርን።”
ሮሜ 8፤36
መስከረም 29 ቀን የምስክርነት በዓልዋ
አንገትዋ በሰይፍ ተከሎ የወደቀችበት
ዐብይ በዓል ነው
የገነት ሙሽራ የወንጌል ፍሬ የወራዙት መቅረዝ የነገሥታት ሥጦታ ያላማለላት የውበት ደም ግባት ከንቱነት በተግባር ያሳየች በአላውያን ነገሥት ውልድ ፍጡር ቤተክርስቲያን ድንጋይ ሎቱ ስብሐት በሚሉ መሐል ቆማ አምላኬ እግዚእነ ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው ብላ የመሰከረች፤
ክብር ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ የክብሩን ጸዳል ያበራባት እናታችን ቅድስት አርሴማ በረከትዋ ይደርብን በቃልኪዳንዋ ትጠብቀን ምልጃ ጸሎትዋ አይለየን።
🙏አሜን አሜን አሜን🙏
💧⚡️እንኳን ለሰማዕተ ክርስቶስ ለቅድስት አርሴማ አመታዊ በዓል አደረሰን✨