༺ ༻
የአባታቸው ስም ስምዖን ፣የእናታቸው ደግሞ አቅሌስያ ይባላሉ። በደቡባዊ ግብፅ ይኖሩ ነበር።በትዳር ሲኖሩ ልጅ ባለመውለዳቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ ልጅ እንዲሰጣቸው ይጸልዩ ነበር ።
ጌታችንም በቅዱስ ወንጌል “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል” ይላል (ማቴ ፯÷፯-፰)
አቅሌስያ እግዚአብሔን የሚፈራ ልጅ፣ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሚሆንልጅ እንዲሰጣት እግዚአብሔርን የማያውቅ ከሆነ ግን ማኅፀኗን እንዲዘጋው ትለምን ነበር።ልጅ እንደምትወልድ ተነግሯት ወደ ቤቷ ተመለሰች።
-የሚሳነው የሌለ እግዚአብሔር ከ30በኋላ መጋቢት ፳፱ ሌሊት የአቅሌስያ ማኅፀን መልካም ፍሬ አፈራ።
በእግዚአብሔር ኃይል የተዘራው ፍሬም አፍርቶ ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ለክርስቲያ ተስፋ የሚሆን ልጅ ተወለደ።ወዲያው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ስሙን ገብረ መንፈስ ቅዱስ አለው።እንደ ተወልዱ ስብሐት ለአብ ፣ ስብሐት ለወልድ ፣ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸውን ፈጣሪ አመስግነዋል።
የእናታቸውንም ጡት ሳይቀምሱ በእግዚአብሔር ተአምር. እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይኖሩ ጀመሩ። ስምዖን እና አቅሌስያም ባዩት ነገር ተደነቁ።በዚህም ሁኔታ ፫ዓ ዓመታት ተቆጠሩ።ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ታዞ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ተቀብለህ ገዳማውያን ወዳሉበት ውሰደውና ከአበምኔቱ በር አስቀምጠው ስለምግቡ እንዳይጨነቁ ፣ምግቡም ቃለ እግዚአብሔር ነው ብለህ ንገር አለው።
ቅዱስ ገብርኤልም ሕፃኑን አቅፎ ወደ ፯ኛው ሰማያት ወስዶ ከእግዚአብሔር ጋር አገናኘው።
እግዚአብሔርም ከእድንግል ማርያምና ከቅዱሳኑ ጋር እንዲገናኙ መልአኩን አዘዘው።መልአኩም መልሶ ወደ አባ ዘመደ ብርሃን ወሰደው ።ሕፃኑን አባ ዘመደ ብእሃን በር ላይ አገኙት፣ደስ ብሏቸውም ተቀበሉት።አስተምረቅ መዓርገ ዲቁና አቡነ አብርሃም ከተባሉ ጳጳስ እንዲቀበሉ አደረጓቸው።
እግዚአብሔር 60 አንበሶችና 60 ነብሮችም አብረዋቸው ይኖሩ ነበር።እነዚህን ምን አበላቸዋለሁ አሉ ጻድቁ? “የረገጥከውን እየላሱ ይጠግባሉ፣ወደ እኔም እስክተመጣው አብረውህ ይኖራሉ” አላቸው።
ከራስ ፀጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸውም ፩ ክንድ ከስንዝር የሚሆን ፀጉር በቀለላቸው።ከሰው ተለይተው ፃድቁ በጫካ ከአናብርትና ከአናብስት ጋር ይኖሩ ጀመር።
በግብፅ ለ፫ ዓመታት ሲጋደሉ ኖረው ወደ ኢትዮጵያ ለመሔድ ተነሡ። ምድረ ከብድ ላይም ለመጀመሪያ ጊዜ እግራቸውን የኢትዮጵያን አፈር ነካ።ከዚያም መልእከ ወደ ደብር ቅዱስ ዝቋላ ወሰዳቸው።
ከባሕር ዳር ቁመው የኢትዮጵያን ሰዎች ኃጢአት ባዩ ጊዜ እጅግ አዘኑ፣ ወደ ባሕር ተወርውረው በመዘቅዘቅ ይጸልዩ ነበር።መልአከ እግዚአብሔር ውጣ ሲላቸው መላውን የኢትዮጵያ ን ሕዝብ ካልማርክልኝ አልወጣምብለው ተጋድሎአቸውን ቀጠሉ። መቶ ዓመታት ያህል በባሕር ወድቀው ከጸለዩ በኋላ ጌታችን ወደ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሄዶ መላውን ሕዝብ ምሬልሃለሁ ውጣ አላቸው።ሰይጣን ሲፀልዩ በቊራ ተመስሎ ፪ቱንም ዐይኖቻቸውን አጠፋቸው።ሳያቋርጡ ፀለዩ ።
ቅዱስ ጳውሎስ ” ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ” እንዲል (፩ ተሰ ፭÷፲፰) እስከ ፯ ሱባኤም እንደ ቆዩ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ወርደው ዐይናቸውን እፍፍ ቢሉባቸው ከቀድሞው የላቀ ብርሃን አገኙ።ወደ ዝቋላ ሂደው መቶ ዓመት ሲዋጓቸው የነበሩትን አጋንንትን አጠፏቸው።
ምንጭ፣÷ ገድለ መንፈስ ቅዱስ
ሐመር መጽሔት ጥቅምት 2008 ዓ/ም
ከጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን።
ምድራዊ መልአክ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ