የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት/ቤት ታሪክ

 • ወጣቶች ዘወትር በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እየተገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት ፣ ሥርዓትና ትውፊት የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነው፡፡
 • የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ማለት የፆታ ፣ የዘር ፣ የቀለም ልዩነት ሳይኖር በየአጥቢያው ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት የሚማሩ ተማሪዎች ማለት ነው፡፡
 • መንፈሳዊያን ወጣቶች ማለት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርት የሚማሩ ሆነው እንደየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ብዛት አንፃር በዕድሜ ደረጃ ተደልድለው ይማራሉ፡፡

የሰንበት ት/ቤት ዓላማ

 • ‹‹ ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዋቸው አትከልክሏቸው ›› ሉቃ 08፣06 /18 ፣ 16 ‹‹ የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ›› መክ 02፣1 / 12 ፣ 1 ፤ በቅዱሳን መጻሕፍት በታዘዘው መሠረት ሕጻናትና ወጣቶች በሰውና በእግዚአብሔር ፊት በጥበብ በሞገስ እንዲያድጉ ፣ ሉቃ 2፣፴9 / 2፣39
 • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ጠብቀው በአባቶች እግር ተተክተው ቤተክርሲቲያንን እንዲረከቡ ለማድረግ መዝ ፵4 ፣ 06 / 44 ፣ 16
 • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲን መንፈሳውያን ወጣቶች በሰንበት ት/ቤት እንዲሰባሰቡና በቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲታነፁ ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መንፈሳዊ ወጣት የሥራ ፍሬ አክብሮትና ታማኝነት እንዲኖረው ለመንፈሳዊ ሥራ ፅኑዕ ፍላጎት እንዲያድርበት ማበረታታት
 • በሥርዓተ አበው በቅዱሳን መጻሕፍት እንደታዘዘው ልጆች ለአባቶቻቸውና በጠቅላላው ለሰው ልጆች ሁሉ ተገቢውን አክብሮት እንዲያሳዩ ለሀገራቸው ፍፁም ፍቅር እንዲኖራቸው ለማድረግ ፣ 1ኛ ጢሞ 5፣02 /5 ፣ 1-2

 

የሰንበት ትምህርት ቤት ታሪክ

 • ከ09፻፵ / 1940 ዓ.ም ጀምሮ የወጣቶች እና የጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበራት ብቅ ብቅ አሉ፤ ይህም ለሰንበት ት/ቤት መመስረት አመልካች ሁኔታ ነበር፡፡
 • በጊዜው ከነበሩት አንጋፋዎቹ ማኅበራት ውስጥ ሃይማኖተ አበው እና ተምሮ ማስተማር ይጠቀሳሉ፡፡
 • መጸሐፍ ቅዱስን እንዲሁም የቅድስት ቤተክርቲያንን ዶግማና ቀኖና ለመማር በየቦታው የሚደረገውን መሰባሰብ ምክንያት በማድረግ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በቃለ አዋዲ መብት በመስጠት በየአጥቢያው የወጣቶች ማኅበር እንዲመሰረት አደረጉ ፡፡
 • በኅዳር ፳9 09፻፸ / 29 1970 ዓ.ም በቃለ አዋዲው በአንቀጽ 07 / 17 ‹‹የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር ›› በሚል ህጋዊ መብት አገኘ፡፡
 • በ09፻፸1 / 1971 ዓ.ም የካቲት 7 / 7 ራሱን የቻለ መምሪያ እንዲኖረው አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የወጣቶች ጉዳይ መምሪያ እንዲቋቋም እና ማኅበራቱ ሁሉ በመምሪያው ስር እንዲተዳደሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡
 • ‹‹የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር››የሚለው ስያሜ እስከ የካቲት 4 1973 ዓ.ም ድረስ ካገለገለ በኃላ ‹‹ የሰንበት ትምህርት ቤቶች›› በሚል እንዲተካ ተደርጓል፡፡ የስያሜው ለውጥ ያስፈለገበትም ምክንያት
  • በጊዜው በነበረው የደርግ መንግስት ከፖለቲካዊ አቋም እና አላማ ውጪ በማኅበራት ስም መደራጀት እንዳይኖር በመከልከሉ እንደሆነ ይታመናል፡፡
 • ይህ መተዳደሪያ ደንብ ለ03 / 13 ዓመታት እስከ ግንቦት 2 09፻፹6  / 2 1986 ዓ.ም ድረስ ካገለገለ በኃላ ግንቦት 3 / 3 ቀን 09፻፹6  / 1986 ዓ.ም ተሸሽሎ ባለ ፴2 /  32 አንቀጽ ሕግ እና ደንብ ጸደቀ፡፡ይህም ህግና ደንብ አሁንም ድረስ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት

09፻፶809፻፷8 /1958-1968 ዓ.ም

የእግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት/ቤት ሚያዚያ 06/16  09፻፶8/1958 ዓ.ም የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር ተብሎ በዛፍ ጥላ ሥር ተመሠረተ፡፡

ይህን መንፈሳዊ ማኅበር የመሰረቱት አባቶችና ወንድሞች

 • በቀድሞው አጠራር አባ ተፈራ መልሴ(በአሁን ንቡረ ዕድ ገ/ሕይወት መልሴ) የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
 • መምህር ሙሉጌታ አሽኔ (መ/ህይወት ሙሉጌታ አሽኔ )                        የማኅበሩ ፕሬዝዳንት
 • መሪጌታ ወልደ ዳዊት ቸኮል የማኅበሩ መምህር
 • አቶ ጌታቸው ንጉሴ የማኅበሩ ም/ፕሬዝዳንት
 • ዲያቆን በቀለ ኪዳኔ ዋና ጸሐፊ
 • አቶ አበበ ማስረሻ ም/ ጸሐፊ
 • መዘምር አሰፋ ግዛው ድርሰት ክፍል
 • አቶ ተስፋዬ ዘለቀ                                                 ግምጃ ቤት
 • አቶ ነጋሽ ገብርዬ አባል
 • መምሬ ማሞ ገ/ጻድቅ አባል
 • አቶ ሠይፈ ገላግሌ አባል
 • ኮ/ል ክፍሉ ደምሴ መዝሙር ክፍል
 • አቶ ዘርጋው ቤተሰብ
 • አቶ ታምራት ቤተሰብ
 • አቶ አበበ ደምሴ
 • ጋሽ ተስፋዬ

 

 • ማኅበሩ ሲመሠረት አባል የነበሩት ወንዶች ብቻ ነበሩ፡፡
 • ሴቶች ከቤት ወደ ቤ/ክ ከመምጣት አልፎ በወጣቶች ማኅበር አባል መሆን የተለያየ ትርጉምና ስያሜ ያሰጥ ስለነበር አይሳተፉም፡፡
 • በኃላ ላይ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የነበሩ አባ ተፈራ መልሴ ለካህናት እና ለምዕመናን በማስረዳት ሴቶች አባል እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ ሴት አባላትም
  • ከበደች ተ/አብ ፣
  • አልማዝ ተ/አብ፣
  • መንበረ ጥላዬ ፣
  • መታሰቢያ ሸዋ ፣
  • አባዬ መቅደስ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
 • የማኅበሩ አባላት በምስረታው በዛፍ ጥላ ስር ፣ ከዚያም በመቃብር ቤት እና በክርስትና ቤት ይሰባሰቡ የነበር ሲሆን የአባላቱ ቁጥር ሲበዛ አዳራሽ ተሠርቷል፡፡
 • በዚህ ወቅት በሰ/ት/ቤት ያገለግሉ ከነበሩት መምህራን መካከል
  • ዲ/ን ኢያሱ (09፻፷/1960 ዓ.ም የሰበካ ጉባኤ ጸሐፊ የነበሩት የአሁኑ ብጹዕ አቡነ ገብርኤል )
  • አባ ኤልያስ(ብጹዕ አቡነ ኒቆዲሞስ /አሁን በሕይወት የሌሉ)
  • ደ/ን ገረመው ሸዋዬ (ለሰ/ት/ቤቱ ከቤተ ክህነት የተመደቡ የመጀመሪያው መምህር)
  • መምህር ወልደ ዳዊት (የግእዝ መምህር)
  • መሪጌታ ወልደ ዳዊት ቸኮል
  • መሪጌታ አብርሃም መኮንን
  • መሪጌታ ብርሃኑ ወደስ
  • መሪጌታ ፀሃይ ብርሃኑ … ናቸው፡፡
 • በየሳምንቱ አምሳ ሳንቲም መዋጮ ያደርጉ ነበር፡፡
 • በደብረ ታቦር በዓል ላይ ጸበል ጻድቅ በማዘጋጀት ለምዕመናን በማደል በዓሉን ያከብሩ ነበር፤ ይህ አገልግሎት እስከ አሁን የቀጠለ ነው፡፡
 • በትንሳኤ ሌሊት እና በማዕዶት ዕለት ነዳያንን መመገብ የተጀመረው በዚህ ጊዜ ነበር፤ ይህም አገልግሎት ሰፍቶ እስካሁን የቀጠለ ነው፡፡

09፻፷82/1968-72 ዓ.ም

የሰ/ት/ቤቱ እንቅስቃሴ በ09፻፷6/1966 ዓ.ም መገባደጃ አገልግሎቱን ያደበዘዘ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ይኸውም በሰ/ት/ቤት ያገለግሉ ከነበሩ ሴቶች የተወሰኑት ካህን ሊያደርገው የሚገባውን የቤተክርስቲያን ቀኖና በመፈጸማቸው በሊቀ ጳጳሱ ተወግዘው ሰ/ት/ቤቱ ለ2/2 አመታት እንዲዘጋ ተደርጓል፡፡

ከሁለት አመት በኃላ በወቅቱ የደብሩ አስተዳዳሪ በነበሩት በአባ ጴጥሮስ በአዲስ መልክ እንደገና ተከፍቷል፡፡

አገልግሎቱ በአዲስ መንፈስ በመቀጠልም በሊቀ ሊቃውንት አባ ተፈራ መልሴ አማካኝነት አሁን የሰ/ት/ቤቱ አባላት የሚገለገሉበት አዳራሽ በማኅበሩ አባላት ጉልህ ተሳትፎ ሊሰራ ችሏል፡፡

ለግንባታው የፈጀው 35000 ብር ሲሆን ከአለም አብያተ ክርስቲያናት ተራድኦ 24000 ፣ከማዘጋጃ ቤት 5000፣ ከእድሮችና ግለሰቦች  ደግሞ 5000 ተሰብስቧል፡፡

የአዳራሹ ግንባታ እንደተጠናቀቀ በዚያን ወቅት የነበረው ቤተ መቅደስ ፈርሶ ታቦተ ህጉ አደራሽ እንዲገባ ስለተደረገ የሰ/ት/ቤቱ መርሐ ግብር በፋፋ ቤት ይካሄድ ነበር፡፡

የካቴድራሉ ግንባታ ሲጀመርም የሁሉም ትኩረት ወደዚያ ሆነና የማኅበሩ አገልግሎት ተዳከመ፡፡ በተጨማሪም በነበረው ርዕዮተ አለም አማካኝነት ከ09፻፸2/1970-72 ዓ.ም የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች የእድገት በህብረት ዘመቻ በመሔዳቸው እንቅስቃሴውን ከፍተኛ በሚባል ሁኔታ ሊያዳክመው ችሏል፡፡

ከ09፻፸2-፹2/1972-82

በዚህ ጊዜ በርካታ መንፈሳዊ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

መሪጌታ ይባቤ ዘመልአክ የሰ./ት/ቤቱ መምህር ሆነው ተመድበው በመምጣት የነገረ መለኮት ትምህርትንና ትርጓሜ ወንጌል ለወጣቱ በሚገባው መልክ በመስጠት በርካታ አባላት ለመምህርነት እንዲበቁ አስችለዋል ፡፡

በመጋቤ ምስጢር ጌድዮን ዘላለም የግእዝ ት/ት መሰጠት ተጀመረ፡፡ በዚህም የግእዝ ቋንቋ ወጣቶች ደፍረው እንዲያነቡ ፣ ግስ እንዲገሰግሱ ያደረጉበት እና ቀላል የንግግር ዘይቤ ሴቶች ሳይቀር የቻሉበት ጊዜ ነበር፡፡

 • ይህም ለዐማኑኤል የመጀመሪያ ት/ቤት መከፈት ምክንያት ሆኗል፡
  • በጋሻው ወ/ሰንበት (የመጀመሪያ ርዕሰ መምህር እና የሰንበት ት/ቤት አባል)
  • ደጀኔ ሽፈራው (የሃይማኖት ት/ት መምህር)
  • ሂሩት አየለ (መዝሙር አስጠኚ እንዲሁም የቀለም ት/ት መምህር)
 • በዚህ ት/ቤት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንዲያሰስተምሩ በጊዜው የነበሩ የሰንበት ት/ቤት ተጠሪዎች ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡
 • በዚህ ት/ት መሰረትነት ብዙዎች ለትልቅ ደረጃ ደርሰዋል ፡፡ የግእዝ መምህርት የሆነችና ለግእዝ መማሪያ የሚሆን መጸሐፍ ያሳተመች ኑኃሚን ዋቅጅራ ፡፡

መምህር ሐረገወይን ጸጋዬ የቁምና የቸብቸቦ መዝሙራትን በብዛት ግጥምና ዜማቸውን በማዘጋጀት በማስጠናት እና የመሐረነ አብ ጸሎት በዜማ በማስጠናት ታላቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ አሁን ሰ/ት/ቤቱ ያሬዳዊ መዝሙርን በተመለከተ ላለው ጹኑ አቋም መሠረቱ ያን ጊዜ የነበረው የመዝሙር ሀብት ነው፡፡

መምህር አምደ ብርሃን የሰ/ት/ቤቱ መምህር በነበሩበት ወቅት በርካታ ወጣቶችን በትምህርተ ሃይማኖት ሊያንጹ  ችለዋል፡፡

መንፈሳዊ ድራማዎች መነባንቦች በማዘጋጀት ለምዕመናን መቅረብ የጀመረበት ጊዜም ነበር፡፡

በመስቀል በዓል የኢትዮጵያን ካርታ በመስራት በመስቀል አደባባይ የመጀመሪያ ትርኢት ከምዕራብ ሰንበት ት/ቤቶች ጋር አቅርቧል፡፡

ለሕጻናትና ማዕከላዊያን ክፍል ይሰጥ የነበረው ት/ት ጠንካራ ነበር፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄና መልስም በተደጋጋሚ ሰ/ት/ቤቱ በአዲስ አበባ ከሚገኙ አድባራት ጋር ተወዳድሮ ብዙውን ጊዜ በማሻነፉ በወቅቱ ከነበሩት ፓትርያርክ እጅ ሽልማት ተቀብሏል፡፡

ከተለያዩ አድባራት እና ሰ/ት/ቤቶች ጋር ግንኙነት ማድረግ ተጀመረ፡፡ሰንበት ት/ቤቱ ከአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ ከሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች ጋር የጠነከረ ግንኙነት ነበረው ፡፡ የዱራሜ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ በመሄድ ኮርስ በማስተማር እና ለአገልግሎት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በመለገስ በተጨማሪም የቤ/ክርስቲያኑ ሕንጻ ሲሰራ በር፣ መስኮት፣ መስታዎት፣ ምንጣፍ፣ እና ለግንባታው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን እርዳታ አድርጓል፡፡

ከእህቶቻችን መካከል ሦስት አባላት ወደ ገዳም ገብተው የመነኮሱበት ጊዜ ሲሆን በአሁን ሰዓት

 • እማሆይ ፍቅርተ ማርያም በቀለ የሰበታ ቤተ ደናግል እመምኔት ፣
 • እማሆይ እህተማርያም ይፍሩ የደብረ ወገግ አባ ሳሙኤል ገዳም እመምኔት ፣
 • እማሆይ ጽጌ ማርያም በግሸን ማርየም በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ ፡፡

ይህ ሁሉ መልካምና በጎ ነገሮች እየተደረጉበት የነበረው ሰ/ት/ቤት ጥቂት አባላት የሃሳብ ልዩነት ምክንያት ሰ/ት/ቤቱ ቀደም ሲል የነበረው አገልግሎት ላይ ጥላውን እንዲያጠላ በማድረጉ አባላት ከሰ/ት/ቤት እንዲርቁ ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህም የአባላት ቁጥር በእጅጉ ቀነሰ፡፡

ከ09፹2-፺

ይህን ጉዳይ ለመፍታት በጊዜው ከነበሩት ታላላቅ ወንድሞች መካከል

መጋቤ ሥርዓት በጋሻው ወ/ሰንበት፣ አቶ ካሳሁን ውርጂ፣ አለማየሁ ነጋሽ፣ አቶ ታደለ ይፍሩ እና አቶ አውላቸው አሻግሬ በሰከነ መንፈስ ሰ/ት/ቤቱን ሊለውጥ የሚችል ሀሳብ በማምጣት ‹‹ የሰ/ት/ቤት ትንሳኤ›› በሚል ቁጥራቸው ከሰባት መቶ በላይ የሆኑ ታዳሚዎች እንዲሁም የቤተ ክህነት ታላላቅ አባቶች በተገኙበት ሚያዚያ//ሐምሌ ፳8 09፹2 / 28 1982 ዓ.ም ታላቅ ጉባዔ ተደረገ፡፡በመጨረሻም የሰ/ት/ቤቱን መዋቅርና ደንብ የሚቀርፅ አጥኚ ቡድን ተዋቅሮ ጉባዔው ተጠናቋል፡፡

ከአንድነት ጉባዔው በኃላ የሰ/ት/ቤቱ መዋቅርና መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ሰባት አባላት ያሉት የሥራ አመራር ኮሚቴና ሶስት አባላት ያሉት የሥነ ሥርዓትና ቁጥጥር  ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገባ፡፡ ይህ ኮሚቴ ወደ ሥራ ሲገባ ያጋጠሙት ችግሮች የቅዳሜና እሑድ መርሐግብር ላይ የተገኙት አባላት ከፍተኛ ቁጥር ፶ (ሃምሳ) ያህል መሆን

የሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት ሦስት በአራት የሚያህል ዙሪያው ቆርቆሮ የሆነ ለስራ ማስኬጃ ፈጽሞ የማያመች ነበር፡፡

የነበሩ ንብረቶች

 • መጸሐፍ ቅዱስ ብዛት ስድስት
 • ዩኒፎርም በሁለት አይነት ቀለም ብዛቱ 50 ከሠላሳ ሁለት ያልበለጠ

ሰ/ት/ቤቱ የነበረው ከፍተኛ የገንዘብ፣ የጽ/ቤት ፣ የጽሕፈት መሳሪያ ችግር በመ/ር ሚሊዮን አሳሳቢነት ከወርልድ ቪዥን ጋር በመተባበር በጊቢው ውስጥ ከነበረው ፕሮጀክት አንድ ሺህ ብር ለሰንበት ት/ቤቱ በመለገሱ የጽሕፈት መሳሪያ ተሟልቶበታል፡፡

ከዚህ በኋላ በተዘጋጀው መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር መሠረት ለትምህርት ክፍል ፣ ለመዝሙር ክፍል ለአባላት ግንኙነት ክፍል ትኩረት በመስጠት ፣ ልዩ ልዩ መርሐግብሮችን በማዘጋጀት አጫጭር  ኮርሶችን በመስጠት ፣ በጠቅላላ ጉባኤ ያሉትን ችግሮች በመፍታት ለውጥ መታየት ጀመረ፡፡

በ09፹4/1984 ለ ሰ/ት/ቤት አንድ መቶ ሃያ የሚደርስ ዩኒፎርም በወቅቱ የነበሩት የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ፀባቴ ተ/ሚካኤል ፋንታሁን ከምዕመናን(ቤት ለቤት በመሄድ) ወደ አስር ሺህ የሚደርስ ብር በመሰብሰብ እና አባላት ራሳቸው በመስፋት ለጥምቀት በዓል አገልግሎት ተሰጥቶበታል፡፡

የተምሮ ማስተማር ኮርስ በወቅቱ በነበሩ የሰ/ት/ቤቱ መምህር አባ ገ/ማርያም አስተባባሪነት ለአንድ ወር ያህል ከሰዋሰወ ብርሃን በመጡ መምህራን ተሰጥቷል፡፡ ይህም ለሦስት ወራት ለሚቆይ መደበኛ ኮርስ መጀመር ምክንያት ሆኗል፡፡

የጽዋ ማኅበራትና የወንጌል ጉባኤያት በሰ/ት/ቤቱ ም/ሊቀመንበር ሥር አንድ ክፍል ሆኖ እንዲዋቀር ተደርጓል፡፡ይህም ከተሃድሶ እንቅስቃሴ ጠብቋል፡፡

የሰ/ት/ቤቱ መደበኛ የጸሎት መርሐ ግብር እና በየወሩ በ፳8 የተጀመረው በዚህ ዘመን ነው፡፡

በ 09፹8 /1988ዓ.ም የሰ/ት/ቤቱ ቤተ መጻሕፍት ከካቴድራሉ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ጋር በመጣመር መንፈሳዊ መጻሕፍትን ከሰ/ት/ቤታችን ዓለማዊ መጻሕፍትን ደግሞ ከት/ቤቱ በማምጣት ተቋቋመ፡፡

09፺-፳፻/1990-2000 ዓ.ም

የሰ/ት/ቤቱ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚሰጠው ትምህርት ቋሚ ሥርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶለት ወደ ተግባር ገባ፡፡

የሰ/ት/ቤቱ የመጀመሪያ መዝሙር ካሴት ታተመ፡፡

የሰ/ት/ቤቱ ሕጻናት እና ማዕከላዊ ክፍል በዕድሜ በመከፋፈል ቀዳማይ፣ ካልዐይ፣ ሣልሳይ፣ አድርጎ በማዋቀርና ሥርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት ለሕጻናት ት/ት መስጠት ቀጥሏል፡፡

አባ ፍቃዱ የተባሉ አባት የነበራቸውን በርካታ መጻሕፍት እንዲደራጅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ፡፡

በ09፺2/1992ዓ.ም ለወረብ አገልግሎት የሚሆን 27 ጥንድ ድርብ ተዘጋጀ፡፡

በአዲስ አበባ ከሚገኙ አኃት ሰንበት ት/ቤቶች ጋር ፣በኢትዮጵያ ከሚገኙ የተለያዩ አድባራት ጋር እንዲሁም ውጭ ሀገር ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ጋር ስኬታማ ግንኙነት የተደረገበ ጊዜ ነበር፡፡

 • በ09፺2/1992ዓ.ም በልደታ ቤተክርስቲያን የተሐድሶ እንቅስቃሴ በነበረበት ጊዜ
  • የሰንበት ት/ቤቱ አባላት ለአንድ ዓመት ዘወትር ምሽት ከ12፡30 እስከ 2፡30 እና እሁድ ከ5-7 በዚህ እንዲሰበሰቡና እንዲማሩ በማድረግ
  • በበዓለ ንግሥ ልደታ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት ፤ የተሐድሶን እንቅስቃሴን ለመግታት ተችሏል፡፡
 • በ09፺2/1992ዓ.ም በተመሳሳይ በገዳመ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ በተነሱ ጊዜ እዚህ መጥተው ዘወትር ቅዳሜ ምሽት እንዲሰባሰቡ በማድረግ እና የበገዳመ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አጥቢያ ምዕመናንን ከሰንበት ት/ቤቱ ጋር በመሰብሰብ የተሐድሶ እንቅስቃሴ እንድገታ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 • የሰ/ት/ ነዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ፡- ሰንበት ትምህርት ቤቱ በየዘመኑ አገልግሎቱን አያሰፋ ሲመጣ አገልግሎቱን ለማስፈጸም በጀት በማስፈለጉ ምክንያት ይኽን ለመሸፈን ሲባል በታችኛው በር በኩል የሚገኘውን ሱቅ ከደብሩ በመከራየት ሐምሌ 1997 ዓ.ም የተለያዩ ነዋያተ ቅዱሳን ምሸጫ ጀምረ የሚመራዉን በዋናዉ ስብሳቢነት ነዉ፡፡
 • በ09፺8/1998 ሰ/ት/ቤቱ ደንብ ማሻሻይ ተደረገበት፡፡

ከ፳፻-8/2000-8ዓ.ም

በ2001ዓ.ም በቤተ መቅደሱ እድሳት ጊዜ የሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽን በመልቀቅ እና ለእድሳቱ የሚያስፈልገውን ብር በማሰባሰብ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ በማበርከት እድሳቱ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በኃላፊነት የጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ የማስለቀቅ ስራ ተረክቦ ለጠበቃ የሚያስፈልገውን ከአባላቱ እና ከሌሎች በጎ አድራጊ ግለሰቦች በመጠየቅ የፍርድ ቤት ሂደቱን በማስቀጠል በዐማኑኤል እርዳታ ከአራት ዓመት በኃላ በ2003ዓ.ም የጻድቃን ሰንበቴ ቤተክርስቲያን እንዲትረከብ አድርጓል፡፡

ከ30 ዓመታት በላይ ያገለገለውን ወንበር በሰ/ት/ቤቱ አባላት፣ደጋፊ ምዕመናን አስተዋጽኦ ከሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በላይ የፈጀ አራት መቶ የሚደርስ ወንበር ተሰራ፡፡የሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ ወንበር ሥራ፡› ቀደመ ሲል አገልግሎት ይሰጥ የነበረዉ የእንጨት ወንበር ነበር፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአባሉ ቁጥር በመጨመሩ እና ያለዉ ወንበር ምቾት የማይሰጥ በመሆኑ ወንበር ይሰራ የሚል አሳብ በመነሳቱ 2003 ሐምሌ ወር ላይ ኮሚቴ በማዋቀር እና እያያንዳዱ አባላት 85 ብር በማዋጣት ከበጎ አድራጊሆች  ደግሞ ድጋፍ በማግኘት አምስት አምስት የተያያዘ 75 ወንበር በድምሩ 350 ወንበር ተሰርቶ በ2004 ዓ.ም ሰኔ ወር ተጠናቆ አገልግሎት  አየሰጠ ይገኛል፡፡

አንድ መቶ ዩኒፎርምና ሰባ ሦስት ጥንድ ድርብ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደረገ፡፡

መስማት የተሳናቸው አባላትን በቋንቋቸው እንዲማሩ መርሐ ግብር ዘርግቷል፡፡

የባለትዳሮች ክፍል ተቋቁማል፡፡

አዲሱን ቢሮ መረከብ ፡ ሰ/ት/ቤቱ ጥበት የተነሳ ለተወሰኑ ጊዜአት ቦታ በመቀያየር ይጠቀም ነበር፡፡በቅርብ ሲጠቀምበት ቆይቶ በጥበቱ ምክንያት አገልግሎት ለመስጠት አመቺ በለመሆኑ ሰ/ት/ቤቱ ለሰበካ ጉባኤ ቢሮ እንዲሰጠዉ ጥያቄ አቀረበ ሰበካ ጉባኤዉም የጥያቄዉን አግባብነት በመመልከት በ2004 ዓ.ም በላይኛዉ በር በኩል ባለዉ ባለ 2ፎቅ ሕንፃ ላይ የመሬት ያለዉን የሚገለገልበትን አዲስ ቢሮ ለሰ/ት/ቤቱ ተሰጠዉ›፡፡

የዐማኑኤል ጠበል የማስከበር ስራ ፡የዐማኑኤል ጠበል በቤተክርስቲያኒቱ ቁጥጥር ስር በመሆን አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ በግቢው ውስጥ ሌላ (የአቡነ አረጋዊ /የኪዳነምህረት) ጠበል በመፍለቁ ምዕመኑ የግቢውን ጠበል መጠቀም በመጀመሩ ወደ ዐማኑኤል ጠበል የሚሄዱ ምዕመናን ቁጥር ቀነሰ፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ጊዜ በሰው ቁጥጥር ስር ከቆየ በኋላ በድጋሚ በ2005 ዓ.ም ተመልሶ በቤተክርስቲያኒቱ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደረገ፡፡በ2007 ዓ.ም ከሰበካ ጉባኤ ጋር በመሆን አባላቱን በማስተባበር ዙሪያው እንዲታጠር እና የቦታው ካርታ ለቤተክርስቲያን እንዲሰጥ አድርጓል፡፡

በ 2007 ዓ.ም የደብሩ ካርታ ጉዳዩን በማስፈጸም እንዲሰጥ አድጓል፡፡

በአሁኑ ወቅት(2008) መቶ አምሳ የሚደርስ ዩኒፎርም ተዘጋጀ፡፡የበፊቱ ዩኒፎርም  15 ዓመት አገልግሏል፡፡ ከአገልግሎት  ጊዜ ብዛት የተነሳ የደከመ በመሆኑ ከማለቁ በፊት በሌላ መተካት ስላስፈለገ አዲስ ዩኒፎርም እንዲስራ በመወሰኑ ከሚቴ በመዋቀር ጠንካር ያለ ስራ ተጀምሮ አባላቱም 116 ብር እንዲከፍል በማድረግ እና ከበጎ አድራጊዎች በመሰብሰብ 150 ዩኒፎርም ተሰፍቷል፡፡

የደም ልገሳ አገልግሎት፡- ሰ/ት/ቤቱ ከሚያከናውናቸው በጎ አድራጎት ሥራ መካከል አንዱ ደም የመለገስ አገልግሎት  ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤቶች  ፈር  ቀዳጅ በመሆን ሰኔ 3 2003 ዓ.ም አባላቱን ግንዛቤ በመስጠትበመጀመሪያ ዙር 50 አባላት ደም ለግሰዋል ደም ለግሰዋል፡፡ በየዓመቱ ግንዛቤ በማስፋት እና ከአባላቱ ባሻገር ምዕመናንም እንዲሰጡ ቅስቀሳ በማድረግ ቁጥሩን ከፍ በማድረግ ተችሏል ፡፡ ሰ/ት/ቤቱን አርዐያ በማድረግ አንዳንድ ሰ/ት/ቤቶች ደም መለገስ ጀምረዋል፡፡ እስካሁን 14 ጊዜ  ደም የመለገስ አገልግሎት ተከናውኗል፡፡ የደም ልገሳው በዓመት 3 ጊዜ ይሰጣል 20003 ዓ.ም ጊዜ አንስቶ እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ አባላት እንዲሁም ምዕመናን ደም መለገስ ችለዋል፡፡ የሰ/ት/ቤቱ ስም በበጎ ለሚያስጠሩ አገልግሎቶች አንዱ ይህ አገልግሎት ነው፡፡

ለተከታታይ እና ለተልዕኮ ትምህርት መስጫ የሚሆኑ 4 የተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍት ታትመው ለአገልግሎት እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት የሚገኙ አባላት ቁጥር ሁለት ሺህ አምስት መቶ ደርሷል፡፡

የሰ/ት/ቤት ፍሬዎች

የአባላት መንፈሳዊነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ጊዜ ነው፡፡

ክፍለ ማርያም ደምሴ፡ ከአባልነት እስከ ሊቀ መንበርነት ደረጃ ሲያገለግል ነበር፤ ይህ ለመናፍቃን ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ብዙ ምዕመናንን ከመነጠቅ የታደገ ነው፡፡ በመጨረሻም ቤት ንብረቱን ትቶ እንደመነነ ይነገራል፡፡

እማሆይ ፍቅርተ ማርያም በቀለ፡ የሰበታ ቤተ ደናግል እመ ምኔት

እማሆይ እህተማርያም ይፍሩ፡ የደብረ ወገግ አባ ሳሙኤል ገዳም እመ ምኔት

እማሆይ ጽጌ ማርያም (አይናለም አስፋው)፡ በጊሸን ማርያም በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ፡፡