# በ09፻5 / 1905 በልጅ ኢያሱ ዘመነ መንግስት ተመሰረተ፡፡

# ፊታ አውራሪ ሀብተ ጊዬርጊስ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሊያሳንጹ አስበው ነበር፡፡

# አፈ ንጉስ ጥላሁን የተከሉት የቀበና አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ስለነበር በዚህ የዐማኑኤል ቤተክርስቲያን እንዲታነጽ ተደረገ፡፡

# የዐማኑኤል ጽላት በመጀመሪያ በጎንደር ክፍለ ሀገር ነበር፡፡

# ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ወደ ቅድስት ሥላሴ አሰመጡት፡፡

# ከቅድስት ሥላሴ ባሻ ተሰማ አማካኝነት መጥቶ በሁለተኛው መቃኞ ገብቷል፡፡ይሀም የሆነው የመጀመሪው መቃኞ ለአገልግሎት አመቺ ስላልነበር ነው፡፡

# የዐማኑኤል ቤተክርስቲያን የተክለሃይማኖት ቤ/ክ ገጠር ነው እየተባለ ይጠራ ነበር

# በ09፻0 / 1910 ዓ/ም ግንቦት ፳8 / 28 ቀን ንግሥት ዘውዲቱ ሦስተኛውን መቃኞ በራስ ብሩ እንዲሰራ አዘዙ፡፡

# የደብረ አሚን እና የዐማኑኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ አባ ወልደ ትንሳኤ ነበሩ፡፡

# አባ አለሙ የመጀመሪያው የዐማኑኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ ናቸው፡፡

# በ09፻፳ / 1920 ዓ/ም በንግስት ዘውዲቱ ትእዛዝ የአዲስ ህንፃ ቤ/ክ ግንባታ ተጀመረ፡፡

# በ09፻፳2 / 1922 ዓ/ም መጋቢት ፳4 / 24 ቀን ንግስት ዘውዲቱ ፍጻሜውን ሳያዩ አረፉ፡፡

# በ09፻፴1 / 1931 ዓ/ም ታህሳስ ፳8 / 28 ቀን ህንፃ ቤ/ክ ተጠናቆ ታቦተ ህጉ ወደ ቤ/ክ ገብቷል፡፡

# በ09፻፷9 / 1969 ዓ/ም ጥር ፳8 / 28 አሁን ያለው ህንፃ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትሪያሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጲያ የመሰረት ድንጋይ ተጣለ፡፡

# በዚያን ወቅት የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት አባ ተፈራ መልሴ ነበሩ

# በ09፻፸8 / 1978 ዓ/ም ተጠናቆ ግንቦት ፳8 /28 ቀን ታቦተ ህጉ አሁን ወዳለው ህንፃ ቤ/ክ ገብቷል፡፡

# በ09፻፹9 / 1989 ሞዛይክ የነበረው ጉልላት በአልሙኒየም የተቀየረ ሲሆን ውስጡም የቀለም እድሳት ተደርጎለታል፡፡

# በ፳፻1/ 2001 አጠቃላይ እድሳት ተደረገለት፡፡በወቅቱ የነበሩት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ተስፋ ፍስሀ ነበሩ

# ሰ/ት/ቤቱ በ፳፻1 / 2001 ዓ/ም አጠቃላይ እድሳት ሲደረግ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ በማበርከት አለኝታነቱን አሳይቷል

# ጥር 9 ፳፻2 / 9 2002ዓ/ም ስራው ተጠናቆ ታቦተ ህጉ ወደ መንበሩ ተመልሷል፡፡