- የቅዱስ መርቆርዮስ ፈረስ ጌታው ከሞተ በኋላ 7 ዓመት በጌታው ተተክቶ አስተምህሮ በጥር 25 ቀን ተገደለ፡፡
- የገላውድዮስ ፈረስ ከአፉ እሳት እየወጣ አሳውያኖችን ያቃትላቸው ነበር፡፡
- የአቡነ አካለ ክርስቶስ መቋሚያ ቤተመቅደስ ሳይታጥን የቀረ እንደሆነ መቋሚያዋ ካለችበት ትሰወራለች፡፡
- የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገዳም በቅሎዎች ተጭነው የ9 ሰዓት መንገድ በርሃ ወርደው ሰው ሳይከተላቸው መንገደኛ ውሃ ቀድቶ ሲጭናቸው ውሃውን ይዘው ለገዳሙ ያስረክባሉ ዛሬም እየተደረገ ነው፡፡
- አቡነ ገሪማ ምራቃቸውን ተፍተው ወደ ጸበልነት የተለወጠች ዛሬም በዋሽነቷ ትታወቃለች፡፡
- ቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጽ 23 ዓመት ፈጀበት በጠቅላላው የሰራቸው አብያተ ክርስቲያናት 210 ናቸው፡፡
- የመጀመሪያው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ቦታ በሰሜን ጎንደር ዳሽን ጣና ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ ገዳም ይባላል፡፡ እርሱንም የሚጠብቀው አውሬ ነው፡፡
- የአቡነ ዘርዓብሩክ ዘጎጃም የተባለው ማየ ጠበል ድርሳኑ ሲደገም ባዶ ጠርሙስ ይቀመጣል፡፡ ድርሳኑ ተደግሞ ሲያበቃ ማሰሮው ጠርሙሶቹ ይሞላሉ፡፡ ያስደንቃል የጸበሉም ስም ረዳኤ ሕይወተ ዘማይ ጸሎት ይባላል፡፡
- ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የእስላም መስጊድ እንዲሰራ ያደረገው ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ይባላል፡፡ ይህም ከግብጽ የመጣው ጳጳስ የፈቀደው በሀገሩ እስላም መንግስት አድልቶ ስለነበር የኢትዮጵያ ሕዝብ አሰቃይቶ አባረረው፡፡
- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ5 እንጀራ በ2 ዓሣ ከሕጻናቱ በስተቀር 5ሺህ ሰው አበርክቶ 12 መሶብ ተርፎ የተነሣበት ዕለት በጥር 28 ቀን ነው፡፡
- አጼ ይኩኖ አምላክና አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሠሩዋቸው አብያተ ክርስቲያናት ብዛት 510 ሲሆኑ 160ው ታላላቅ ገዳማት ናቸው፡፡
- ጌታችን 99ኙን ነገደ መላእክት ትቶ አንዱን የጠፋው አዳምን ሊፈልግ እንደመጣ የሚያትተው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሉቃስ ወንጌል 15፡13 ነው፡፡
- ንጉስ ቆስጠንጢንዮስ በሰኔ 12 ቀን በ312 ዓ.ም በአዋጅ የጣዖታትን ቤት ዘግቶ ቤተክርስቲን እንድትከፈት አደረገ፡፡
- በመጽሐፈ ኩፋሌ እንደተጠቀሰው የኖኅ ሚስት አምዛይ የሎጥ ሚስት ሚልካ የአብርሃም እናት ዲና ይባላሉ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
ከቤተ መጻሕፍት

