- “የወጡ ማጣፈጫ ቅቤ ነው፡፡ የሃይማኖት ማጣፈጫ ግን ምግባር ነው፡፡”
- “ክርስትና እያዘኑ የሚደሰቱበት ሃይማኖት ነው”፡፡
- “ለአጢያት ንስሐ መግባት ሕይወት ነው፤ አለመግባት ግን ሞት ነው”፡፡
- “መንፈሳዊ መካሪ ርካሽ ሳይሆን ውድ ነው”፡፡
- “መጽሐፍ ቅዱስ ምግብ ነውና ይመገቡት”::
- “መጽሐፍ ቅዱስ ያብሩት ብርሃን ነውና”፡፡
- “ለጠቢብ ሰው ምላስ ጤና ናት”፡፡
- “የጠቢብ ሰው ከንፈር እውቀትን ትዘራለች”፡፡
- “የጻድቃን በደል በአንደበታቸው ነው፤ የኃጥአን በደል ግን በመላ ሰውነታቸው ነው”፡፡
- “ሰው ለሚለው ነገር እንቢ ማለት በሽታ ነው”፡፡
- “በሰው ንግግር መቀለድ ቂላቂልነት ነው፡፡”
- “መነሳቱን የሚያውቅ ሰው መውደቁን እያቀደ ነው፡፡”
- “መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት መዝገብ ቃል ነው፡፡”
- “ፆም ራስን ሠውነትን የሚያሳይ መስታወት ነው፡፡”
- “ፆም የነፍስ ቁስል ትፈውሳለች፡፡”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!
ምንጭ፡ – አትሮንስ መጽሐፍ

