- “በየጊዜው ለንስሐ መራኹ” (ቅዱስ እንጦንስ)
- “ፈሪሐ እግዚአብሔር ከሌለ ንስሐ የለም፡፡”
- “ቁጡ ብስጩ አትሁን ቁጣ ነፍስ ወደማጥፋት ይደርሳል፡፡” /ቅዱስ እንድርያስ/
- “ቂም በቀል የሌለህ ሁን ቂም በቀል በሌላቸው ሰዎች መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉና” /ቅዱስ ታዴዎስ/
- “ከኃይልና ከጩኸት ይልቅ ይቅርታና ትህትና ጠንካራ ናቸው፡፡”
- “ኃጢአት መደበቅ በራሱ ኃጢአት ነው፡፡”
- “እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በተፈጥሮ ያልሰጠውን ማንም ሊሠጠው አይችልም፡፡”
- “በራሱ ለራሱ አመኔታ ከሌለው ከሰው ቁምነገር መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡”
- “የዲያቢሎስ አንዱ መንገድ ሰውን በፀጋው ማኩራራት ነው፡፡”
- “የዶሮ እርግማን ጭልፊቷን አያስጨንቃትም፡፡”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!
ምንጭ፡ – አትሮንስ መጽሐፍ

