ይህን ያውቁ ኖሯል

  • የቅዱስ መርቆርዮስ ፈረስ ጌታው ከሞተ በኋላ 7 ዓመት በጌታው ተተክቶ አስተምህሮ በጥር 25 ቀን ተገደለ፡፡
  • የገላውድዮስ ፈረስ ከአፉ እሳት እየወጣ አሳውያኖችን ያቃትላቸው ነበር፡፡
  • የአቡነ አካለ ክርስቶስ መቋሚያ ቤተመቅደስ ሳይታጥን የቀረ እንደሆነ መቋሚያዋ ካለችበት ትሰወራለች፡፡
  • የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ገዳም በቅሎዎች ተጭነው የ9 ሰዓት መንገድ በርሃ ወርደው ሰው ሳይከተላቸው መንገደኛ ውሃ ቀድቶ ሲጭናቸው ውሃውን ይዘው ለገዳሙ ያስረክባሉ ዛሬም እየተደረገ ነው፡፡
  • አቡነ ገሪማ ምራቃቸውን ተፍተው ወደ ጸበልነት የተለወጠች ዛሬም በዋሽነቷ ትታወቃለች፡፡
  • ቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጽ 23 ዓመት ፈጀበት በጠቅላላው የሰራቸው አብያተ ክርስቲያናት 210 ናቸው፡፡
  • የመጀመሪያው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ቦታ በሰሜን ጎንደር ዳሽን ጣና ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ ገዳም ይባላል፡፡ እርሱንም የሚጠብቀው አውሬ ነው፡፡
  • የአቡነ ዘርዓብሩክ ዘጎጃም የተባለው ማየ ጠበል ድርሳኑ ሲደገም ባዶ ጠርሙስ ይቀመጣል፡፡ ድርሳኑ ተደግሞ ሲያበቃ ማሰሮው ጠርሙሶቹ ይሞላሉ፡፡ ያስደንቃል የጸበሉም ስም ረዳኤ ሕይወተ ዘማይ ጸሎት ይባላል፡፡
  • ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የእስላም መስጊድ እንዲሰራ ያደረገው ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ይባላል፡፡ ይህም ከግብጽ የመጣው ጳጳስ የፈቀደው በሀገሩ እስላም መንግስት አድልቶ ስለነበር የኢትዮጵያ ሕዝብ አሰቃይቶ አባረረው፡፡
  • ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ5 እንጀራ በ2 ዓሣ ከሕጻናቱ በስተቀር 5ሺህ ሰው አበርክቶ 12 መሶብ ተርፎ የተነሣበት ዕለት በጥር 28 ቀን ነው፡፡
  • አጼ ይኩኖ አምላክና አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሠሩዋቸው አብያተ ክርስቲያናት ብዛት 510 ሲሆኑ 160ው ታላላቅ ገዳማት ናቸው፡፡
  • ጌታችን 99ኙን ነገደ መላእክት ትቶ አንዱን የጠፋው አዳምን ሊፈልግ እንደመጣ የሚያትተው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሉቃስ ወንጌል 15፡13 ነው፡፡
  • ንጉስ ቆስጠንጢንዮስ በሰኔ 12 ቀን በ312 ዓ.ም በአዋጅ የጣዖታትን ቤት ዘግቶ ቤተክርስቲን እንድትከፈት አደረገ፡፡
  • በመጽሐፈ ኩፋሌ እንደተጠቀሰው የኖኅ ሚስት አምዛይ የሎጥ ሚስት ሚልካ የአብርሃም እናት ዲና ይባላሉ፡፡

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

ከቤተ መጻሕፍት

ሆሣዕና (ለሕፃናት)

በቤካ ፋንታ

መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም

በኢየሩሳሌም በምትገኝ በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ነው የምኖረው፡፡ ከተወለድኩ አምስት ዓመት ሞልቶኛል፡፡ በዕለተ ሰንበት በቤት ውስጥ እየተጫወትሁ፣ እናቴም በጓዳ ሥራ እየሠራች ሳለን በድንገት የብዙ ሰዎች የዕልልታ ድምፅ በሰፈሩ ውስጥ ሰማን፡፡ እናቴም በፍጥነት ከጓዳ ሮጣ ወጥታ ‹‹ልጄ! ልጄ! ነይ እንሒድ!›› ብላ አዝላኝ እየሮጠች ከቤት ወጣች፡፡ በኹኔታው ተገርሜአለሁ፡፡

በሰፈር ውስጥ ያሉ ጓደኞቼ ዅሉ በእናቶቻቸው ጀርባና በአባቶቻቸው ትከሻ ላይ ኾነው ከወላጆቻቸው ጋር በደስታ ዕልል ይላሉ፡፡ የሕፃናቶቹን ብዛት ሳይ ይበልጥ ተደሰትሁ፡፡ የሚያለቅስ አንድም ልጅ የለም፡፡ ‹‹ዛሬ የሕፃናት የደስታ እና የዝማሬ ቀን ነው›› ብሎ ልቤ በደስታ ፈነደቀ፡፡ ወላጆቻችን ዅሉ የዘንባባ ዝንጣፊ እየቈረጡ ያዙ፤ ለእኛም ሰጡን፡፡ ከዚያ ዕልል እያልን በደስታ ወደ ቤተ መቅደስ ሮጥን፡፡

በመንገድ ላይ በጣም ብዙ ሕዝብ አየሁ፤ እነርሱም ዘንባባ ይዘው ደስ ብሏቸው እንደኛ ወደ ቤተ መቅደስ ይሮጣሉ፡፡ በመካከላቸው አንድ ትልቅ አህያ አየሁኝ፣ ከአህያይቱም ጋር ውርንጫዋ (ልጇ) አለች፡፡ የሚያማምር ልብስ በአህያዎቹ ጀርባ ላይ ተነጥፏል፡፡ በውርንጫዋም ላይ የዅላችን ፈጣሪ፣ ንጉሣችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀምጦ ስመለከት በደስታ ዘለልሁኝ፡፡

ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መኾን በጣም ያስደስታል፡፡ ምክንያቱም እርሱ እኛ ሕፃናትን እቅፍ አድርጎ ስሞን በጉልበቱ ላይ ቁጭ አድርጎ ያስተምረናል፣ ይመክረናል፡፡ በዙሪያውም ላሉት ሰዎች ‹‹እንደነዚህ ሕፃናት ንጹሓን ኹኑ፤ ኃጢአት አትሥሩ፤›› እያለ ይመክራቸዋል፡፡

ከዚያ ዕልል እያለ የሚያመሰግነው ሕዝብ፣ እንደዚሁም በእናትና በአባቶቻችን እቅፍ ውስጥ ያለን ሕፃናት በአንድነት ኾነን ጮክ ብለን የዘንባባውን ቅጠል እያውለበለብን መዝሙር መዘመር ጀመርን፡፡ መዝሙሩም እንዲህ የሚል ነው፤ ‹‹ሆሣዕና በአርያም ለዳዊት ልጅ፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፡፡ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፡፡›› የመዝሙሩ ድምፅ በኢየሩሳሌም ከተማ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተሰማ፡፡ በጣም ደስ ያለኝ ደግሞ የእኛ የሕፃናቱ ድምፅ ከትልልቆቹ በልጦ መሰማቱ ነው፡፡

ጌታችንን በአህያዋ ላይ ተቀምጦ ባየሁት ጊዜ ትዝ ያለኝን አባዬ መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበ ያስተማረኝን ታሪክ ልንገራችሁ፤ ታሪኩም፡- ‹‹አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺየኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ ዕልል በዪ! እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ኾኖ በአህያ፣ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፤›› የሚል ነው (ትንቢተ ዘካርያስ ፱፥፱)፡፡

የዝማሬውን ድምፅ ሲሰሙ አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወዱት በከተማው ውስጥ ያሉ ጨካኝ ሰዎች ወደ እኛ መጡ፡፡ ሰዎቹም ሕዝቡ ዅሉ ደስ ብሏቸው እየዘመሩ፣ ዕልል እያሉ፣ የዘንባባውን ቅጠል እያውለበለቡ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገኑ ወደ ቤተ መቅደስ ሲሔዱ በተመለከቱ ጊዜ ተናደው ሕዝቡን ‹‹ዝም በሉ!›› ብለው ተቈጧቸው፡፡ ሕዝቡም ፈርትው ዝም አሉ፡፡

እኔና ጓደኞቼ ግን በእናታችን ጀርባ ላይ ካሉት ሕፃናት ጋር አብረን ኾነን ጮክ ብለን ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› የሚለውን መዝሙር ሳናቋርጥ እንዘምር ነበር፡፡ የገረመኝ ደግሞ ከእኔ የሚያንሱ ሕፃናትም መዝሙሩን ጮክ ብለው ሲዘምሩት መስማቴ ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ መናገር የማንችለውን እኛን እንድንዘምርልህ ስለፈቀድህልን ተመስገን!›› ብዬ አምላኬን አመስግኜ መዝሙሩን መዘመር ቀጠልሁኝ፤ ‹‹ሆሣዕና፣ ሆሣዕና፣ ሆሣዕና በአርያም …፡፡››

በኋላ ግን እነዚያ ጨካኞቹ ሰዎች ስላስፈራሯቸው ወላጆቻችን ዝም አስባሉን፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በአህያዋ ውርንጫ (በትንሿ አህያ) ላይ ቁጭ ብሎ ለጨካኞቹ ሰዎች ‹‹ከሕፃናት ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሴ አዘጋጅቻለሁ፡፡ የእነርሱንም አፍ ይዛችሁ ዝም ብታስብሏቸው በዙሪያዬ ያሉት ድንጋዮች ያመሰግኑኛል፤›› አላቸው፡፡

ከዚያም ጌታችን፡- ‹‹የፈጠርኋችሁ ድንጋዮች ሆይ! ሕፃናት እንደ ዘመሩ እናንተም በመዝሙር አመስግኑኝ፤›› በማለት በታላቅ ድምፅ ሲናገር ግዙፍ ድንጋዮች ከመሬት ወደ ላይ እየተነሡ ‹‹ሆሣዕናበአርያም ለዳዊት ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና እናቀርባለን …›› እያሉ በሚያስደስት ድምፅ እየመዘመሩ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ በዚህ ጊዜ ጨካኞቹ ሰዎች አፍረውና ፈርትው ተመለሱ፡፡

እኛ ሕፃናት፣ ወላጆቻችንና በዙሪያችን የነበሩ ድንጋዮችም አምላካችንን ከበን በዕልልታ እየዘመርን፤ ለአህያዎቹ መርገጫ ልብሳችንንና የዘንባባውን ዝንጣፊ እያነጠፍን ወደ ቤተ መቅደስ ገባን፡፡ በዚያም ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደስ የሚል ትምህርት አስተማረን፡፡

በመጨረሻም ‹‹ሆሣዕና›› ብለን ምስጋና ላቀረብነውና በቤተ መቅደስ ተገኝተን ቃሉን ለምንሰማው ሕፃናት ጌታችን እንዲህ ብሎ መከረን፤ ‹‹ልጆቼ በመዝሙራችሁ ተደስቻለሁ፡፡ ዅል ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን እየመጣችሁ ዘምሩልኝ፡፡ በአንደበታችሁ በመዝሙር አግዚአብሔርን አመስግኑበት እንጂ ዘፈን እንዳትዘፍኑበት፡፡ ዘፈን ኃጢአት ነው፡፡››

ትምህርቱን ተከታትለን ከእናቴ ጋር ደስ እያለን ወደ ቤታችን ተመለስን፡፡ ታዲያ ዅል ጊዜ ይህችን የሆሣዕናን በዓል በውስጤ አስባታለሁ፤ መዝሙሩን መዘመር በጣም ያስደስተኛል፡፡ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻ የመከረኝንም ምክር ጠብቄ ዘፈን የሚባል በአፌ ሳልዘፍን በመዝሙር እግዚአብሔርን እያመሰገንሁ አደጌአለሁ፡፡

ልጆችዬ! ዛሬ የምታነቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩ ከቍጥር ፩ እስከ ፲፮ እና የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፩ ከቍጥር ፩ እስከ ፲፯ ያለው ትምህርት ነው፡፡

‹‹ሆሣዕና በአርያም›› ብለን እንድናመሰግነው የፈቀደልን፤ ኃይሉን ጥበቡን የሰጠን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

“ሰላምን ሻት ተከተላትም”(መዝ.፴፫፥፲፬)

በመ/ር ኃይለ ሚካኤል ብርሃኑ
ሰላም ማለት ጸጥታ፣ ዕረፍት፣ እርጋታ፣ እርካታ ማለት ሲሆን የእርስ በእርስ ስምምነት በአንድነት አብሮ መኖር መቻልና የዕረፍት ስሜት እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ያስረዳል፡፡ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “ሰላምን ሻት ተከተላትም” ብሎ ከመናገሩ አስቀድሞ የመጽሐፉን ክፍል ወደ ኋላ መለስ ብለን የተነሳንበትን ኃይለ ቃል ሙሉ አሳቡን ለመረዳት ስንመለከተው እንዲህ የሚል ቃል እናገኛለን፡፡ “ልጆቼ ኑ ስሙኝ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችሁ ዘንድ፤ ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው? አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈሮችህም ሸንገላን እንዳይናገሩ ከክፉ ሽሽ መልካንም አድርግ ሰላምን ሻት ተከተላትም” ይላል፡፡
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሰላምን የምንሻበትን ምክንያት በዚሁ በተመለከትነው ኃይለ ቃል ላይ ገልጦታል፡፡ እንደ አባትነቱ እግዚአብሔር ልጆቹ ለምንሆን ለእኛ ሊያስተምረን የፈቀደለትንና እርሱ በሕይወቱ ገንዘብ አድርጎት በእግዚአብሔር እንደ ልቤ ተብሎ የተመረጠበትን ጥበብ ለእኛም ሲያካፍለን “እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁአለ፡፡ምክንያቱም እግዚአብሔርን መፍራት ከሁሉ ይልቅ ቀዳሚ ነውና፡፡ ለዚህም ነው አባትና ልጅ ተባብረው(ተቀባብለው) የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት እንደሆነ የነገሩን(መዝ. 111፥10፣ምሳ.1፥7፣9፥10)፡፡
ከሁሉ አስቀድሞ በሕይወታችን እግዚአብሔርን መፍራት ትርጉም ላለው ሕይወት አስፈላጊ ነው፡፡ ሰላምን የምንሻበት መንገድ እሱ ነውና፡፡ ቅዱስ ዳዊት እግዚአብሔርን መፍራት ሕይወትን የሚያስገኝና በጎ ዘመንን ለማየት የምንችልበት የጥበብ (የዕውቀት) ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ይህንንም ከገለጸ በኋላ “ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው? ብሏል፡፡ ከላይ እንዳየነው ሕይወትን ለማግኘት የሚሻ በጎ ዘመንንም ለማየት የሚፈልግ ጥበብን (ማስተዋልን) ገንዘብ ያደረገ ሰው ነው፡፡ በመሆኑም ሕይወትን ለማግኘትና በጎ ዘመንን ለማየት የሚሻ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት ስንመለከትም ቅዱስ ዳዊት እንደነገረን ቀጥለን በዝርዝር እንመለከታቸዋለን፡፡
፩ኛ አንደበትን ከክፉ መከልከል
የሰው ልጅ በልቡ ያሰበውን በአንደበቱ ይናገራል፡፡ በልብ የታሰበውን መልካምም ይሁን ክፉ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ነገር ግን የታሰበው ነገር በውጫዊ ሰውነት ላይ በሚታዩ ምልክቶች (ገጽን በማየት) መታወቅ የሚችልበት አጋጣሚ ከተፈጠረ ወይም በአንደበት ቢነገርና በሥራ ቢተገበር ሰዎች ይረዱት ይሆናል፡፡
ይሁንና አንደበትን ከክፉ ካልከለከሉት ሰዎችን የሚጎዳና የማይሽር ጠባሳ ጥሎ የማለፍ በዚያም ሰበብ ተናጋሪውን ሳይቀር ሁለተኛውን አካል በቁጣ በመጋበዝ ለሞት የማብቃት ዕድል አለው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ “ምላስ እሳት ናት እነሆ ትንሽ ምላስ በሰውነታችን ውስጥ ዐመፅ የተመላበት ዓለም ናት ሥጋችንን ትበላዋለች ውስጣዊ ሰውነታችንንም ትጠብሰዋለች ከገሃነምም ይልቅ ታቃጥላለች” ይላል፡፡
ስለዚህ ሕይወትን የሚፈቅድና በጎ ዘመንን ለማየት የሚፈልግ ሰው አንደበቱን ከክፉ ነገር መከልከልና መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ ተናግሮ ሰውን ላለማስቀየምና ላለማስከፋት መጠንቀቅ አለበት፡፡ ሌላውንም ሰው ወደ ጥፋት ላለመምራት ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ አንደበት ኃያል ነውና ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይበልጣል የሚል አባባል እንዳለ እናስታውሳለን፡፡
አንደበትን ከክፉ ካልከለከልነው ስድብንና ሐሜትን እናበዛለን፡፡ ይህ ደግሞ ከሕይወት ጎዳና የሚያወጣ ክፉ ተግባር ነው፡፡ በጓደኛ መካከል፣ በባልና ሚስት መካከል፣ በአንድ ሀገርና በሌላው ሀገር መካከል፣በጎሳና በጎሳ መካከል ፣ በጎረቤትና በጎረቤት መካከል ሐሜትና መነቃቀፍ፣ ስድብና ጥላቻ ካለ በጎ ዘመንን ማየት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ሕይወትንም ሆነ በጎ ዘመንን ለማየት አንደበትን ከክፉ መከልከልና በጎ ነገርን ማውራት አስፈላጊ ነው፡፡
፪ኛ. ከክፉ መሸሽ
ከክፉ መሸሽ ማለት ክፉን ከማድረግ መቆጠብና ክፉ ከሚያደርጉት ጋር በክፋታቸው አለመተባበር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ሁል ጊዜም ቢሆን ከክፉዎች ጋር ኅብረት የለውም አባታችን ያዕቆብ ልጆቹን በሚመርቅበት ጊዜ ክፉ ሥራ ከሠሩ ከልጆቹ የክፋት ሥራ ጋር እንደማይተባበርና ከክፋት ጋር ኅብረት እንደሌለው ገልጧል፡፡ “ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ በጭቅጭቃቸውና በጦራቸው ዐመጽን ፈጸሟት በምክራቸው ሰውነቴ አትገናኛቸው አሳቤም በአመጻቸው አትተባበርም በቊጣቸው ሰውን ገድለዋልና በገዛ ፈቃዳቸውም የሀገርን ሥር ቆርጠዋልና ቁጣቸው ርጉም ይሁን ጽኑ ነገርና ኩርፋታቸውም ብርቱ ነበርና በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ” (ዘፍ.49፥5)
ያዕቆብ ምንም እንኳ በሥጋ የወለዳቸው ልጆቹ ቢሆንም በፈጸሙት ክፉ ሥራ ግን እንደማይተባበር ከክፉ ሥራቸው የራቀና ከክፋት የተለየ መልካም አሳብ እንዳለው ገልጧል፡፡ ዛሬም ቢሆን የሰው ልጆች ክፋትና በደል እየበዛ ባለበት ሰዓት የእግዚአብሔር ልጆች ከክፋት፣ ከተንኮል፣ ከውሸት፣ ከሌብነት፣ ከቅሚያ፣ ከዝርፊያ፣ ከጭካኔ፣ ከሴሰኝነት፣ ከዘማዊነት፣ ከዘረኝነት በአጠቃላይ ለራስም ለሀገርም ከማይበጁ እኩይ ምግባራትና ከሚፈጽሟቸው ሰዎች ጋር መተባበር የለብንም፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደነገረን ሕይወትን ለማግኘት የምንሻና በጎ ዘመን ለማየት የምንፈልግ ሁሉ ከክፉዎች ጉባኤ መለየትና አለመተባበር ያስፈልጋል፡፡
፫ኛ. መልካም ማድረግ
ሕይወትን ለማግኘትና በጎንም ዘመን ለማየት የሚሻ ሰው ሁሉ መልካምን ሁሉ ሊያደርግ ያስፈልገዋል፡፡ ከክፉ መሸሻችንና ከከፉዎች ጋር አለመተባበራችን መልካም ሥራ ለመሥራት መሆን አለበት እንጂ ከሥራ ርቀን እንዲሁ እንድንኖር አይደለም፡፡ያለ በጎ ሥራ መኖር ስንፍና ነውና፡፡
እግዚአብሔር የሰውን ውድቀቱንና መጥፋቱን የማይሻ አምላክ ስለ ሆነ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በክፉ ሥራ ተጠምዶ የነበረ ሁሉ ሊመለስና በሕይወት ሊኖር ይገባዋል፡፡ በቀደመው ስሕተቱ ወንድሙን ያሳዘነ፣ሰው የገደለ፣አካል ያጎደለ፣ ግፍን የፈጸመ፣የድሃውን ገንዘብ በተለያየ ሰበብ የዘረፈ፣ጉቦ የተቀበለ፣በነዚህና መሰል እኩይ ሥራዎች ሀገሩን የጎዳ፣ እግዚአብሔርን የበደለ ሁሉ ከልብ በመጸጸት በልቅሶና በዋይታ ወደ እገዚአብሔር መመለስ ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህም አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በነቢዩ ሕዝቅኤል ላይ አድሮ ኃጢአተኛው ከኃጢአቱ ተመልሶ በሕይወት መኖር እንዳለበት አስገንዝቦናል፡፡
“እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው (በደለኛው) ይሞት ዘንድ አልፈቅድም ይላል ጌታ እግዚአብሔር፡፡የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ ከከፉ መንገዳችሁ ተመለሱ ስለምንስ ትሞታላችሁ? (ሕዝ.33፥11) እንዲል፡፡
እግዚአብሔር በነቢዩ ላይ አድሮ እንደ ነገረን በደለኛ ሰው በበደሉ ቀጥሎ መጥፋት የለበትም፡፡መመለስና በሕይወት መኖር ያስፈልገዋል እንጂ፡፡ እሱም እንደ በደሉ ዓይነት የቅርታ ጠይቆ፣ ንስሓ ገብቶ፣ የበደለውን ክሶ፣ የሰረቀውን መልሶ፣ የሰበረውን ጠግኖ፣ ያጎደለውን መልቶ በፍጹም መጸጸት ሊመለስና መልካም በመሥራት ሌት ተቀን ከሚተጉት ጋራ በመልካም ሥራ ሊተባበር ያስፈልገዋል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን “ስለዚህ ሐሰትን ተውአት ሁላችሁም ከመንገዳችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ እኛ አንድ አካል ነንና አትቆጡ አትበድሉም ፀሐይ ሳይጠልቅም ቊጣችሁን አብርዱ ለሰይጣንም መንገድን አትስጡት የሚሰርቅም እንግዲህ አይስረቅ ነገር ግን ድሃውን ይረዳ ዘንድ በእጆቹ መልካም እየሠራ ይድከም” (ኤፌ. 4፥25) ይላል፡፡
ሰላምን መሻት
ሰላም ለሁሉ ነገር አስፈላጊና ሁሉን ለማድረግ የምንችልበት የመልካም ነገር ሁሉ በር ነው፡፡ ሰላምን መፈለግ ሕይወትን ለማግኘትና በጎ ዘመንንም ለማየት ያስችላል፡፡ በአይነቱ ሰላምን በሁለት መልኩ እናየዋለን፡፡ እሱም የውስጥ ሰላምና የውጭ ሰላም ወይም ውስጣዊ ሰላምና ውጫዊ ሰላም ብለን እንመድበዋለን፡፡
የሰው ልጅ ለመኖር ውስጣዊ ሰላምም ሆነ ውጫዊ ሰላም ያስፈልጉታል፡፡ ውስጣዊ ሰላም የምንለው አንድ ሰው ከፍርሐት፣ ከጭንቀት፣ ከመረበሽ፣ ከሥጋትና ወዘተ ነጻ ሆኖ መኖር ሲችል ውስጣዊ ሰላም አለው ይባላል፡፡ ይህም የውስጥን ሰላም ከሚያደፈርሱ፣ አእምሮን ከሚረብሹ፣ ልብን ከሚያቆስሉ፣ የጸጸት እሮሮን ከሚያስከትሉ ነገሮች ስንርቅና ለአእምሮ የሚመች ሥራ ስንሠራ ውስጣችን ሰላም ይሆናል፡፡ውጫዊ ሰላም የምንለው ደግሞ፡- ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከጎረቤት፣ ከሀገራት ጋር ተስማምተንና ተግባብተን ተቻችለንና ተረዳድተን በፍቅር ተሳስረን መኖር ነው፡፡ በመሆኑም ሰላም ከጥል፣ ከመለያየት፣ ከመጠላላት፣ ከመገፋፋት፣ ከመነቃቀፍ ተቆጥበን የጠብንና የጦርነትን ወሬ ባለመስማትና በስምምነት ተግባብቶ በመኖር የሚገለጥ ነው፡፡ ስለዚህ ሰላም ለሁሉ እንደሚያስፈልገው ካወቅን የሰላም መገኛ ማን እንደሆነና ሰላም ከየት እንደሚገኝ ማወቅ ደግሞ አስፈላጊ ነው፡፡

የሰላም መገኛ
ሰላም የሚገኘው የሰላም ባለቤት ከሆነው ከልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንደገለጠው እውነተኛ ሰላም ከእግዚአብሔር ይገኛል፡፡ እርሱ የሰላም አምላክ ነውና (ሮሜ. 15፥33)፡፡ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም አለቃ ተብሏል፡፡ “ሕፃን ተወዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘለዓለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ. 9፥6) እንዲል፡፡
ዓለም ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ያህል ሰላሙን አጥቶ በመቅበዝበዝ ይኖር የነበረ ሲሆን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን፣ መሞትና መነሣት እውነተኛውን ሰላም አግኝቷል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ሞት ምክንያት ፍርሐት ጸንቶባቸው ለነበሩት ደቀ መዛሙርት “ሰላምን እተውላችኋለሁ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም ልባችሁ አይደንግጥ አትፍሩም (ዮሐ.14፥27) በማለት ፍርሐትን፣ ስጋትን፣ ጭንቀትን፣ ሁከትን፣ መረበሽን የሚያርቀውን (የሚያስወግደውን) እውነተኛውን ሰላም አደለን፡፡
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት እንዳለው ሕይወትን ለማግኘትና በጎ ዘመንን ለማየት የምንሻ ሁሉ ሰላምን መሻት ያስፈልጋል፡፡ ደግሞም ሰላምን መሻት ብቻ ሳይሆን መከተል ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም መሻት ብቻውን ዋጋ ሊኖረው ስለማይችል፡፡ መሻታችን ወደ ማግኘት የሚደርሰው የምንሻውን ነገር ለማግኘት ወደ መገኛው መጓዝና መቅረብ ሲቻል ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰላምን ሻት ካለ በኋላ ተከታላትም በማለት በሰላም መንገድ መጓዝ፣ የሰላም ወሬ ማውራት፣ ለሰላም የሚስማማ ሥራ መሥራት የራሳችን ሰላም መጠበቅና የሌላውንም ሰላም አለማደፍረስ ማለት እንደሆነ የነገረን፡፡በሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየተሰማ ያለው የሰላም ዜና፣እየዘነበ ያለው ሰላም ፣እየተጠረገ ያለው የሰላም መንገድ ለዚሁ ማሳያ ነው፡፡ በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ተራርቀው የነበሩ ሁለት አካላት የሚያለያያቸውን የጥላቻ ድንበር አፍርሰው የሚያገናኛቸውን የፍቅር ድልድይ መመሥረት አንዱ የሰላም መንገድ የሰላም መገለጫ ነው፡፡
ወደ ቤተ ክርስቲያን አባቶችም ስንመጣ ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት ተለያይቶ የነበረው ቅዱስ ሲኖዶስ ልዩነቱን እንደ ውበት ቆጥሮ ወደ መቀራረብና ወደ አንድነት ጉባኤ ለመምጣት የዘረጋው የሰላም መድረክ አንዱ የሰላም መገለጫ ነው፡፡ስለዚህ እንደ ግል ከራስ ጋር ተስማምቶ፣እንደ ሀገር በሀገር ውስጥ ካሉት ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር ተግባብቶ መኖር የሚያስችሉትን የፍቅር መረቦች መዘርጋት የሰላም መንገድ፣ ሰላምን መሻትና መከተል ነው፡፡
የእግዚአብሔር ሰላም ለሁላችን ይሁንልን፡፡ አሜን
ምንጭ፤ሐመር መጽሔት 26ኛ ዓመት ቁጥር 3 ሐምሌ 2010ዓ.ም

የሰንበት ት/ቤት ትርጉም

  • ወጣቶች ዘወትር በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እየተገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት ፣ ሥርዓትና ትውፊት የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነው፡፡
  • የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ማለት የፆታ ፣ የዘር ፣ የቀለም ልዩነት ሳይኖር በየአጥቢያው ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት የሚማሩ ተማሪዎች ማለት ነው፡፡
  • መንፈሳዊያን ወጣቶች ማለት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርት የሚማሩ ሆነው እንደየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ብዛት አንፃር በዕድሜ ደረጃ ተደልድለው ይማራሉ፡፡

Continue reading “የሰንበት ት/ቤት ትርጉም”

የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት/ቤት ታሪክ

በቅድስት ቤ/ክ ታሪክ ውስጥ የሕጻናት እና የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህም ቤ/ክ ወጣቶችን በማስተማር ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ካላት ፅኑ ፍላጎትና እምነት ነው፡፡

ከ 1940 ዓ.ም ጀምሮ የወጣቶች እና የጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበራት ብቅ ብቅ አሉ፤ በጊዜው ከነበሩት አንጋፋዎቹ ማኅበራት ውስጥ ሃይማኖተ አበው እና ተምሮ ማስተማር ይገኙበታል፡፡

አሁን ያለበትን መልክ ይዞ እንዲጓዝ መሰረት የጣሉ ባወጡትም ቃለ አዋዲ መብት የሰጡት ሁለተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ናቸው፡፡

በ1971 ዓ.ም በመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የወጣቶች ጉዳይ መምሪያ እንዲቋቋም እና ማኅበራቱ ሁሉ በመምሪያው ስር እንዲተዳደሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ፡፡

በ1973 ዓ.ም ኅዳር 29 የወጣቶች መንፈሳውያን ማኅበር በሚል ስያሜ ህጋዊ መብት አግኝቷል፡፡ Continue reading “የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት/ቤት ታሪክ”

የደብሩ ታሪክ

# በ09፻5 / 1905 በልጅ ኢያሱ ዘመነ መንግስት ተመሰረተ፡፡

# ፊታ አውራሪ ሀብተ ጊዬርጊስ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሊያሳንጹ አስበው ነበር፡፡

# አፈ ንጉስ ጥላሁን የተከሉት የቀበና አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ስለነበር በዚህ የዐማኑኤል ቤተክርስቲያን እንዲታነጽ ተደረገ፡፡

# የዐማኑኤል ጽላት በመጀመሪያ በጎንደር ክፍለ ሀገር ነበር፡፡

# ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ወደ ቅድስት ሥላሴ አሰመጡት፡፡ Continue reading “የደብሩ ታሪክ”

ድረገጽ

ይህ ተግባራዊ ድረገጽ በጥናቱ ግኝት መሰረት የሰንበት ትምህርት ቤታችንን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ያማከለ እና በጥናቱ መጀመሪያ ላይ የቀረቡትን ስጋቶች እና ደካማ ጎኖችን ተሻግሮ የታለመለትን አላማ ሊያሳካ በሚችል አቅም የተዋቀረ ነው፡፡ ይህ ድረገጽ በቀጣይ ሂደቶች ውስጥ አቅሙን ሊያሻሽሉ የሚችሉ አስፈላጊ የሆኑ የይዘት እና የቅርጽ ማሻሻያዎች ሊደረጉበት ይችላል፡፡ ይህ ተግባራዊ ድረ ገጽ በዋናነት ከሌሎች ድረገጾች በተሻለ አዳዲስ ነገረችን ያቀፈ ሲሆን በዋነነትም በማንኛውም የኤሌክትሮኒክ የግንኙነት መንገድ ማለትም በስልክ (አንድሮይድ ወይም አይ.ኦ.ኤስ) እንዲሁም በኮምፒውተር ያለምንም ችግር መጠቀም የሚያስችል አቅም ተፈጥሮለታል ይህም በስልክ (አንድሮይድ ወይም አይ.ኦ.ኤስ) ተደራሽ የሚያደርጋቸውን ምዕመናን ቁጥር ከፍ ያደርገዋል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ የተደረጉ ገጽታዎችን በሌሎች ክፍች እንመለከታቸዋለን፡፡ Continue reading “ድረገጽ”

ኸረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ

የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ

ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ከንስሐ ሸፈተ

መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ነፍሴ በኀጥያት ሸተተ

እምቢ አለኝ ጾም ጸሎት አምቢኝ አለኝ ንስሐ

ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከአለም ውሃ Continue reading “ኸረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ”

ዕርቅ

ቤተ ክርስቲያን ይህንን ሰሞን ከዕርቅና ከፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ወገኖችን የሐሳብ ፍጭት እያስተናገድች ትገኛለች፡፡ አንድ ሰው የቱንም ዓይነት ሐሳብ ይኑረው ለቤተ ክርስቲ ያን ይበጃል ብሎ ሐሳብ እስከሠነዘረ፣ ያንን ሐሳቡንም ከሸፍጥና ከሰይጣናዊ መንገድ በተለየ መልኩ ባገኘው የተረፈቀደ መድረክ ላይ ሁሉ እስካንጸባረቀ ድረስ ለቤተ ክርስቲያን ይበጃል እንጂ አይጎዳትም፡፡ ቀደምት አበው የቤተ ክርስቲያንን አመራር ከግለሰባዊነት ይልቅ ለጉባኤ የሰጡበት አንዱ ምክንያት ውይይት፣ ክርክርና የሐሳብ ልዩነት እንዲኖር ብለው ነው፡፡ አንድ ሰው በተመደበበት የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነትና በተፈቀደለት የአገልግሎት ሜዳ ውስጥ ይበጃል ያለውን ሐሳብ ማንሣት፣ ለሐሳቡም ማስረጃ አቅርቦ መከራከር፣ በስተመጨረሻም በጉባኤው ሕግ መሠረት ለጸደቀው ሐሳብ መገዛት ይጠበቅበታል፡፡ በ51 ዓም በኢየሩሳሌም የተደረገችው የመጀመርያዋ የቤተ ክርስቲያን ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ ምክንያት በክርስቲያኖችና እነርሱንም በሚመሩና በሚመግቡ አባቶች መካከል በተነሣው የሐሳብ ልዩነት ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከአይሁድ ማኅበረሰብ ወጥታ ወደ አሕዛብ መንደር ስትገባ በአሕዛብና በአይሁድ ክርስቲያኖች መካከል ከአነዋወራቸው
የተነሣ የሓሳብ ልዩነት ተፈጠረ፡፡

Continue reading “ዕርቅ”

ደቂቀ ሰይጣን

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ (14261460ዓ ም) በዘመናቸው አምልኮ ጣዖትን አስቆማለሁ ብለው ቆርጠው ተነሥተው ነበር፡፡ ይህንን ነገር ለማስቆምም ሦስት ዓይነት መንገድ ለመጠቀም አሰቡ፡፡ መምህራንን እየላኩ ሕዝቡን ለማስተማር፣ ለማስተማርያ የሚሆኑ ድርሰቶችን እንዲዘጋጁ ለማድረግና ራሳቸውም ለማዘጋጀት፣ በመጨረሻ ደግሞ ከዚህ ሁሉ የተሻገረውን ለመቅጣት፡፡ በተለይም በአምልኮ ጣዖት የተያዙትን፣ ይህንንም አምልኮ ከሕዝቡ ገንዘብ ለመሰብሰብና ሕዝቡን ለማታለል ሲሉ የሚያካሂዱትን ሰዎች የሚከታተሉ፤ ባለሥልጣናቱ በድብቅ ይህንን ተግባር ሲያከናውኑ፣ አንዳንድ ካህናትም ከሁለቱም ወገን ሆነው ሲያጭበረብሩ፣ ታዋቂ የሆኑ ሰዎችም በዚህ ባዕድ አምልኮ ውስጥ ሲነከሩ እየተከታተሉ ለንጉሡ መረጃ የሚሰጡ ሦስት ሰዎችን መድበው ነበር፡፡ ዘርዐ ክርስቶስ፣ ተዐውቀ ብርሃንና ገብረ ክርስቶስ የሚባሉት እነዚህ ሦስት ሰዎች ወደ ባዕድ አምልኮ የሚሄዱትን፣ በድብቅ ይህንን ተግባር የሚያከናውኑትን፣ በተለይም የቤተ መንግሥት ሰዎች ሆነው ለሕዝቡ የባዕድ አምልኮ ክፉ አርአያ የሚሆኑትን እንዲጠቁሙ፣ ተከታትለውም እንዲያሲዙ፣ አስይዘውም እንዲያስቀጡ ንጉሡ ሥልጣን ሰጥተዋቸው ነበር፡፡