በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጥር 21 በዓለ ንግሥ የት የት ይከበራል?

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኙ በእነዚህ ገዳማትና አብያተ ክርስትያናት የጥር 21 (አስተርእዮ ማርያም) ዓመታዊ የንግሥ በዓል ይከበራል።

1) ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ካቴድራል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አጠና ተራ

2) አውግስታ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ

3) ፍኖተሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ብርጭቆ ኮንዶሚንየም

4) ማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ የሺ ደበሌ

5) ኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤልና ኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ መሳለሚያ

6) ደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል አደባባይ

7) ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጉርድ ሾላ

8)ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማያት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አባዶ

9)የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጎሮ

10) አንቆርጫ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አንቆርጫ

11) ቦሌ ኆህተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ገርጂ

12) መሪ ቅድስት ሥላሴ፤ቅዱስ ዑራኤል፤ቅድስት ድንግል ማርያም፤ቅዱስ ጊዮርጊስ ወአቡነ አረጋዊ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ መሪ

13) ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም አብያተ ክርስትያናት

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ፈረንሳይ 41 ኢየሱስ

14) ርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፡-ጉለሌ /ክ/ከ እንጦጦ ማርያም

15) መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

ልዩ ስም፦አራዳ ክ/ከ አምስት ኪሎ

16) ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አራዳ ክ/ከ አርበኞች መንገድ
ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል

17) ቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም

18) ብሔረ ፅጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያምና መድኃኔዓለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ብሔረ ፅጌ

19) ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ታቦት ማደሪያ

20) ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ ልደታ

21) ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል ፍላወር

22) ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት ማርያም

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጀሞ 3
መስታወት ፋብሪካ ጀርባ

23) ሐመረወርቅ ቅድስት ማርያም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ

ልዩስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 5 ወርቁ ሰፈር

24) ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ለቡ(ፉሪ)

25) ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ፈጬ

26) ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ሰርጢ ማርያም

27) ቂሊንጦ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ድንግል ማርያም

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 9 ቂሊንጦ

28) ካራ ቆሬ ደብረ ገነት ቅዱስ እስጢፋኖስ፤ቅዱስ ሚካኤልና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ ካራ ቆሬ ጥላሁን ሜዳ

29) መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል

ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ፋኑኤል ሰፈር

30) የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሾላ መገናኛ

31) ደብረ ፅጌ ቅዱስ ኡራኤል

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ካዛንቺስ

32) አፍሪካ ሕብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦ቂርቆስ ክ/ከ አፍሪካ ህብረት

33) ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል፤ቅድስት አርሴማ እና አቡነ አዳም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ ጀርመን አደባባይ

34) አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ጋራው መድኃኔዓለም

35) ቃሊቲ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ ሰፈረ ገነት

36) ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም:- ፈጬ ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒየም ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

37) የጎፋ መካነ ጅያዋን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ቄራ ጎፋ ማዞሪያ ፤ ጎፋ ገብርኤል አደባባይ

38) አያት ቅዱስ ዮሐንስ እና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ።

አድራሻ ፦ አያት ዞን ስምንት በእድገት ጮራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገባ ብሎ

39) በሻሌ ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ።

አድራሻ ፦ ቦሌ በሻሌ ሰንሻይን ሪል ስቴት ጀርባ

40) ብሥራተ ወንጌል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ።

አድራሻ ፦ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ዘነበወርቅ ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ

41) ባህታዊ በሻሌ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ።

አድራሻ ፦ ሰሚት 72 አከባቢ

42) ቦሌ አራብሳ ቃጥላ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ።

አድራሻ ፦ አያት በሻሌ 40/60 ኮንዶሚኒየም አከባቢ

43) አያት ጨፌ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ስውሯ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ።

አድራሻ ፦ አያት 49 ጨፌ ኮንዶሚኒየም አከባቢ

44) ቦሌ አራብሳ ኆህተ ብርሃን ጨፌ ጫንጮ ዋሻ ቤዛዊት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም ቂርቆስ አደባባይ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ገባ ብሎ

45) አራብሳ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ቦሌ አራብሳ ሰፈራ አደባባይ አዲሶቹ ኮንዶሚኒየም አከባቢ

46) የጎሮ ሰፈራ ወይን አምባ ቅድስት ድንግል ማርያም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ጎሮ ሰፈራ (ከጎሮ አደባባይ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ሲወርዱ ትገኛለች)።

47) ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ጋርመንት ሰፈራ አደባባይ አከባቢ

48) ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ጋርመንት ሰፈራ ሃይሆንዳይ ሞተር ፊትለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

ታኅሣሥ 28፦የቅዱስ ዐማኑኤል የንግሥ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የት የት ይከበራል❓

✨እንኳን ለአምላካችን ለቅዱስ ዐማኑኤል የልደት በዓል በሰላም አደረሰን። ✨

የቅዱስ ዐማኑኤል የንግሥ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በየትኞቹ ገዳማት አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል❓

1) አስኮ መካነ ህይወት ቅዱስ አማኑኤል እና አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስ  ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ አዲስ ሰፈር

2) ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦አዲስ ከተማ/ክ/ከ መሳለሚያ እህል በረንዳ

3) ቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አባ ሳሙኤልና ቅዱስ አማኑኤል

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቡልቡል 40/60 ኮንዶሚኒየም ከፍ ብሎ ።

4) ካራቆሬ ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ካራቆሬ ጀሞ ሁለት ኮንዶሚኒየም አከባቢ

5) ደብረ አራራት ማኅበረ በኵር ቅዱስ አማኑኤል አንድነት ገዳም

አድራሻ ፦ የካ ክ/ከ ኮተቤ ከኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ከፍ ብሎ

6) ደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ የካ ክ/ከ ኮተቤ አንድ ፌርማታ አከባቢ ከውሃና ፍሳሽ ታንከር ከፍ ብሎ

7) ገደራ መካነ ብርሃን ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ አያት ጣፎ ኮንዶሚኒየም አከባቢ።

8) ብሔረ ጽጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያም እና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ን/ላ/ክ/ከ ብሔረ ጽጌ

10) ፉሪ ደወለ አይነከረም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ን/ላ/ክ/ከ ጋርመንት ሠፈራ ታክሲ መውረጃ በቀኝ በኩል ገባ ብሎ

🌸🌸መልካም በዓል🌸🌸

ታኅሣሥ19-በአዲስ አበባ በየትኞቹ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት በዓለ ንግሡ ይከበራል?

ቅዱስ ገብርኤል ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን።

በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በእነዚህ አብያተክርስትያናት ታኅሣሥ 19 ሊቀመላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነበት በዓለ ንግሡ ይከበራል።

1) ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ካቴድራል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አጠና ተራ

2) ድልበር መካነ ጎልጎታ መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ጉለሌ ድልበር

3) አስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ

4) ኮልፌ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ፊሊዶሮ

5) ደብረ ቀራንዮ መድኃኔአለም እና ገብርኤል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቀራንዮ

6) ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ እና ቅዱስ ገብርኤል

ልዩ ስም፡- አዲስ ከተማ ክ/ከ ዊንጌት ት/ቤት

7) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦አዲስ ከተማ/ክ/ከ አውቶብስ ተራ

8) ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦አዲስ ከተማ/ክ/ከ መሳለሚያ እህል በረንዳ

9) ቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ እግዚአብሔር አብ

10) ኮተቤ ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤልና ኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ መሳለሚያ

11) የረር ጎሮ ደብረምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ጎሮ

12) አንቆርጫ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አንቆርጫ

13) ቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ገርጂ

14) መንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል

ልዩ ስም፦አራዳ /ክ/ከ ቤተመንግስት

15) ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔአለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ መድሃኔአለም

16) አንቀፀ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ራስ ካሳ

17) ደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ 01 ራሽያ ኤምባሲ ጀርባ

18) ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ /ክ/ከ ፈረንሳይ ብረት ድልድይ

19) ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ ቡልቡላ

20) ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጎፋ

21) አየር ጤና አንቀፀ ብርሃን ቅድስት ኪዳነምሕረት

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አየር ጤና

22) ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ታቦት ማደሪያ

23) ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ብስራተ ገብርኤል

24) አዲስ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና ደብረ ፍስሐ ቅዱስ ገብርኤል

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ሳሪስ አዲስ ሰፈር

25) ፉሪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጋራ ኦዳ

26) ጀሞ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጀሞ

27) ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ላፍቶ

29) ደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ ቂርቆስ

30) ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል፤ቅድስት አርሴማ እና አቡነ አዳም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ ጀርመን አደባባይ

31) አለም ባንክ ጀሞ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አለም ባንክ

32) ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ፈጬ

33) ጃቴ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምሕረት ካቴድራል

ልዩ ስም፦አቃቂ ክ/ከ 08

34) መጠሊ ደብረ አሮን ፍልፍል ዋሻ ቅዱስ ገብርኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስትያን

ልዩ ስም፦አቃቂ /ክ/ከ ገላን ጉዳ ገበሬ ማኅበር መጠሊ አካባቢ

35) ቂሊንጦ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ድንግል ማርያም

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 9 ቂሊንጦ

36) ብስራተ ወንጌል ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን

ልዮ ስም፦ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ዘነበወርቅ ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ

37) መንበረ ልዑል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ን/ስ/ላ/ክ/ከ 58 ማዞሪያ

38) አየርጤና ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 02 አየርጤና

39) የቃሊቲ መካነ ብርሀን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ አ/ቃ/ክ/ክ ወረዳ 07 ማረሚያ ጎን

40) ቱሉ ዲምቱ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አ/ቃ/ክ/ከ ልዩ ስሙ አለም ባንክ

41) ቀበና ምዕራፈ ፃድቃን አቡነ ተክለሃይማኖት እና ቅ/ገብርኤል ቤተ- ክርስትያን

ክ/ከተማ :የካ

ልዩ ቦታ:ሲግናል አደባባይ ወደ ዉስጥ ገባ ብሎ ወይም አድዋ ድልድይ ፖሊስ ጣቢያዉ ወረድ ብሎ ልዩ ስሙ ኮንጎ ሰፈር

42) ደብረ መንክራት መድኃኔአለም እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

አድራሻ:- ቃሊታ ውሃ ልማት ወረዳ 5 በርታ

43) ኤርቱ ሞጆ መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ኤርቱ ሞጆ አከባቢ ።

44) እንዶዴ ሔቹ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ አቃቂ እንዶዴ ፣ እንዶዴ የባቡር ጣቢያ

45) እንቁ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ፉሪ ለቡ ባቡር ጣቢያ ተሻግሮ ጋራው ላይ

46) የየካ ጣፎ መካነ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ፡ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ አያት ጣፎ ኮንዶሚኒየም አከባቢ

47) ገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ገላን ጉራ ፤ ከቦሌ ቡልቡላ ጀርባ ተንጠልጣይ ድልድይ ተሻግሮ

48) ሰሚት መካነ ሕይወት ዋሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ፡ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ ከመገናኛ ሰሚት ኮንዶሚኒየም ሁለተኛ በር የሚለው ታክሲ በመያዝ መጨረሻ ላይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ወደ ዋሻ ቅዱስ ገብርኤል መሄድ ይችላሉ

49) ቦሌ በሻሌ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርአል ቤተ ክርስቲያን ። (ሙት አንሳ ቅዱስ ገብርኤል)

አድራሻ ፦ ቦሌ በሻሌ ኮንዶሚኒየም ጀርባ

50) አያት ጨፌ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

አድራሻ ፦ አያት ጨፌ ኮንዶሚኒየም አከባቢ

ዕረፍቱ ለአቡነ ሀብተማርያም

📚ኅዳር 26

በዚህችም ቀን የተመሰገነና የከበረ ንጹሕም የሆነ የኢትጵያዊ አባታችን የሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡

የዚህ ቅዱስ አባት የትውልድ ሀገሩ የራውዕይ በምትባል በስተምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ነው። በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ሰው ነበር። ይህም ክቡራንና ታላላቅ ከሚባሉት ከዚህች ሀገር ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ እጅግ ሀብታም ነበር፤ ብዙ ንብረትም አለው። በሕጋዊ ጋብቻም ስሟ ዮስቴና የምትባል ብላቴና ድንግልን አገባ፤ ይህችም የተመረጠች በበጎ ሥራ የተሸለመችና ያጌጠች ናት፡፡

ነገር ግን አስቀድመን በዚህ ዓለም ከሕግ ባሏ ጋር በንጹሕ ጋብቻ እግዚአብሔርን በመፍራት ምጽዋትን በመስጠት የዋኅነትን፣ ትሕትናን፣ ፍቅርን፣ ትዕግስትን ገንዘብ አድርጋ በጾም በጸሎት ተወስና እንደኖረች እንነግራችኋለን፡፡

አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያምም በባሕር መካከል በመቆም የዳዊትን መዝሙር ሁሉንም ያነባል፤ በባሕር ውስጥም ሰጥሞ ግንባሩ አሸዋ እስኪነካው አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳል። ከሰንበት ቀኖችም በቀር እህል አይቀምስም ነበር። ከዚህም በኋላ እህልን ትቶ እንደ ዋልያዎች የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ፡፡

ዓርባ ዓርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀን የሚጾምበት ጊዜ አለ። ባሕር ውስጥ በሌሊት ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ያነባል፤ ሌሎች መጻሕፍትንም በእንዲህ ያለ ሥራ ብዙ ዘመን ኖረ፡፡

ብዙ ተጋድሎንና ድካምንም ባስረዘመ ጊዜ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱም ተገልጦ መጣ። ከእርሱ ጋርም የመላእክት አለቆች የከበሩ ሚካኤልና ገብርኤል የመላእክት ማኅበርም ሁሉ በዙሪያው ሁነው እያመሰገኑት ነበር። “ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሰላም ለአንተ ይሁን” አለው፡፡ በዚያንም ጊዜ ከግርማው የተነሣ ወድቆ እንደ በድን ሆነ። ጌታችንም በከበሩ እጆቹ አንሥቶ እፍ አለበትና “ጽና ኃይልህን ላድሳት እንጂ ላጠፋህ አልመጣሁምና። ተጋድሎህና ድካምህ ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰማያዊት እንደተጻፈ በእውነት እነግርሃለሁ፡፡

  እነሆ አኔ በጎ ዋጋህን በዚህ ዓለም በሚመጣውም ዓለም እከፍልሃለሁ፤ የማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል በምታነብ ጊዜ በተራራዎችና በዋሻዎች በፍርኩታ ተሠውረው ወደሚኖሩ እንዳንተ ካሉ ቅዱሳን ጋር ለመገናኘት በላዩ ተቀምጠህ ወደ ምሥራቅ ወደ ምዕራብ ወደ ሰሜንና ደቡብ የምትበርበት የብርሃን ሠረገላ ሰጠሁህ። ሉቃስና ዮሐንስ የጻፉትን ወንጌል ባነበብክ ጊዜ ሥጋዬንና ደሜን በዚያ ትቀበል ዘንድ በላዩ ተቀምጠህ ወደ ኢየሩሳሌም የምትሄድበት የእሳት ሠረገላ ሰጠሁህ” አለው፡፡

ከብዙ ዘመናትና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ የሚሞትበት ጊዜ ሲደርስ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ “ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ዛሬ ግን የመጣሁት ከድካም ወደ ዕረፍት ልወስድህ ነው። እነሆ ሰባት አክሊላትን አዘጋጅቼልሃለሁና፤ አንዱ ስለ ድንግልናህ፣ ሁለተኛው ዓለምንና በውስጡ ያለውን ሁሉን ትተህ በመውጣትህ፣ ሦስተኛው ፍጹም ስለሆነው ምንኵስናህ፣ አራተኛው አራቱን ወንጌሎች አዘውትረህ የምታነብ በመሆንህ፣ አምስተኛው ስለ እኔ ፍቅር መራብና መጠማትን ስለታገሥህ፣ ስድስተኛው በልብህ ቂምና በቀልን ባለማሳደርህ፣ ሰባተኛውም ስለ ንጹሕ ክህነትህና ስለምታሳርገው ያማረ የተወደደ ዕጣንህና መሥዋዕትህ ሰጠሁህ። እነዚህ ሰባቱ አክሊላትም ለእያንዳንዳቸው ዐሥራ አምስት ዐሥራ አምስት ኅብር አላቸው።

መታሰቢያህን ካደረጉና በጸሎትህ ከተማጸኑ ጋር የምትገባበትን ቤት በውስጧ አምስት መቶ የወርቅ ዐምዶች የተተከሉባትን ሰጠሁህ። ደግሞ የእሳት መስቀልን የወርቅ ጫማን የብርሃን ልብስን ሥውር የሆነ መናን እሰጥሃለሁ” አለው፡፡

  መድኃኒታችንም ይህን ቃል ኪዳን ሲሰጠው በየነገዳቸውና በየሥርዓታቸው ዘጠና ዘጠኝ የመላእክት ሠራዊት መጥተው “ወዳጃችን ሰላም ለአንተ ይሁን! ዛሬስ ከፀሐይ ሰባት እጅ ወደምታበራ ሀገራችን በዝማሬና በማኅሌት አክብረን ልንወስድህ መጣን” አሉት፡፡ አባታችን  ሀብተ ማርያምም “በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ሆነ፤ የሰው ነጻነቱ ሊሰጠው” አለ፡፡

ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየውና “የመጥምቁ ዮሐንስን ሀገር ተጠጋግታ ያለች ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ ሀገርን እሰጥህ ዘንድ በራሴ ማልኩልህ” አለው፡፡

“መታሰቢያህን የሚያደርገውን፣ በስምህ ለቤተክርስቲያን መባዕ የሚሰጠውን፣ ስምህን የጠራውን ወደዚህች ሀገር አገባዋለሁ፤ ዓራቱን ወንጌሎችም እያነበብክ ስለኖርክ የየአንዲቱን ቃል ፍሬዋን እንደ አንድ ሺህ አደረግሁልህ፤ ይኸውም ከአንተ በኋላ ለሚመጡ ልጆች መጽሐፈ ገድልህን ለሚያነቡና በእምነት ለሚሰሙ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበበት ውኃ ለሚረጩ ለሚነከሩበት ይህን ቃልኪዳን ሰጥቼሃለሁ፡፡

ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን አፉን ሦስት ጊዜ ሳመው በዚያንም ጊዜ ከፍቅሩ ጣዕም ብዛት የተነሣ ነፍሱ ከሥጋዋ ተለየች፤ ጌታችንም ተቀብሎ አቅፎ ከእርሱ ጋር አሳረጋት፡፡ በመላእክት ጉባኤም ብዙ ምስጋና ተደረገ፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር፤ 

ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ።

ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት



❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በግእዝ ልሳን በእንግልጣር Mercurius በጽርዕ Ἅγιος Μερκούριος, በቅብጥ Ⲫⲓⲗⲟⲡⲁⲧⲏⲣ Ⲙⲉⲣⲕⲟⲩⲣⲓⲟⲥ; በሲርያክ: ܡܳܪܩܘ̇ܪܝܘ̇ܣ; ተብሎ ይጠራል። የተወለደው በምሥራቅ ታሕታይ እስያ በቀጶዶቅያ በአኹኗ ቱርከሰ በ224 ዓ.ም. ሲኾን ወላጆቹ ክርስቲያኖች ሲኾኑ ስሙን ፒሉፓዴር Philopater ብለውታል ትርጓሜውም በግሪክኛ “የአብ ወዳጅ” ማለት ነው። በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል።

❖ በ17 ዓመቱ የሮማን ሰራዊት ተቀላቀለ “ወተውህቦ ኀይል ዐቢይ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ወተሰምዐ ዜናሁ በኲሉ ወተለዐለ እምሰብአ ቤተ መንግሥት” ይላል። ታላቅ የድል አድራጊነት ኀይል እንደ ዳዊት ተሰጥቶት ዜናው በኹሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችን ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚኽ ምክንያት ከ249-251 የሮማ መሪ በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ በ17 ዓመቱ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡

❖ ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት የጸና ነበርና ንጉሡን “እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ አለውና አትፍራ” አለው፡፡

❖ “ወእምዝ ርእዮ ቅዱስ መርቆሬዎስ ለመልአከ እግዚአብሔር በውስተ ቀትል ወሰይፍ በሊኅ ውስተ እዴሁ” ይላል፤ የእግዚአብሔር መልአክ በውጊያው ውስጥ የተሳለ የሚያበራ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግኽ ጊዜ ፈጣሪኽ እግዚአብሔርን ዐስበው” ብሎ ሰጥቶታል፤ አንዱ ራሱ ለውጊያ የያዘው ሰይፍ ኹለተኛም ከመልአኩ የተቀበለው ሰይፍ ነበርና በዚኽ ምክንያት “አበ አስይፍት” (የሰይፎች አባት፤ Abu-Seifein) በዐረብኛ Abu-Sayfain, Abu-Sifin ወይም أبو سيفين, በቅብጥ ⲁⲃⲩⲥⲉⲫⲁⲓⲛ ሲኾን በኹሉም ፍቺው ተመሳሳይ ነው።

❖ ከዚኽ በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ ለጣዖታት ዕጣን ሊያቀርብና በዓልን ሊያደርግ ወደዶ በዓልን ባደረገ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን ከርሱ ጋር አልወጣም፤ በዚኽ ምክንያት ንጉሡ አስጠርቶት “ለአማልክት ዕጣን ለማሳረግ ከእኔ ጋር ያልወጣኽ የእኔንስ ፍቅር ለምን ተውኽ?” ብሎ ጠየቀው፤ በዚኽ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሡ ፊት ትጥቁንና ልብሱን ወርውሮ “እኔ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም” በማለት መለሰለት፡፡

❖ ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ይህንን ሁሉ በክርስቶስ ስም ተቀበለ።

❖ ከመሬት ከፍ ከፍ ያሉ ሁለት ምሰሶ ላይ እንዲታሰር አደረጉት። በችንካር ቸንክረው ገላውን በስል ምላጮች ቆራርጠውታል። ከዚያም ወደ እስር ቤት ቢከቱትም በወኅኒ ቤት ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾ ሰውነቱን በዳሰሰው ጊዜ ተፈውሷል።

❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ኾነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክ አድርጎ በዚያም ብዙዎች ሥቃያትን አደረሱበት።

❖ ከዚያም አንገቱ እንዲቆረጥ ሲወሰን እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ መጸለይ ጀመረ። አምላካችን ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በታላቅ ግርማ ተገለጸለትና “የተወደድክ ልጄ መርቆሬዎስ ወደ ዘላለማዊ ዕረፍትህ ከቅዱሳን ጋር ና፤ ጸሎትህ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን ወደ እኔ ዐረገ፤ የአንተን ስም በያዘ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ተአምር ይደረጋል፤ በአንተ ምልጃ የሚማጸኑኝን እጠብቃቸዋለሁ፤ የአንተን ዜና ገድል የሚጽፉትን የሚያነቡትን ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ” ብሎ ቃል ኪዳንን ገባለት።

❖ ከዚህ በኋላ ጌታችን ቅዱስ መርቆሬዎስን ባረከው፤ ያን ጊዜ በጣም ተደሰተና አንገቱን እንዲቆርጡ የታዘዙት ጋር በፍጥነት ሄዶ ከንጉሡ የታዘዙትን ፈጥነው እንዲፈጽሙ ለመናቸው። ተንበርክኮ “ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው” ብሎ ጸለየላቸው። ከዚያም በተወለደ በ25 ዓመቱ በኅዳር 25 ቀን በ250 ዓ.ም. ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት በክርስቶስ ስም የሰማዕትነትን የክብር አክሊል ተቀዳጀ፤ የሰማዕታት ዘመን ካለፈም በኋላ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውለታልና፡፡

❖ ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈጣን ተራዳኢነቱ የሚታወቅ ሲኾን ከሓዲው ዑልያኖስ ታላላቆች ሊቃውንት የነበሩትን ቅዱስ ባስልዮስንና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ሊገድላቸው በመጣ ጊዜ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ቆመው ቢማፀኑ ቅዱስ ጴጥሮስ ሐናንያና ሰጲራን በሞት እንደቀጣ፤ ቅዱስ ጳውሎስ የበርያሱስን ዐይን እንዳጨለመ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ስም እንደጣለው ቅዱስ መርቆሬዎስም በተራዳኢነቱ እንደ ጎልያድ የታበየውን ክርስቶስን የካደው ከ361 – 363 ድረስ የመራውን ዑልያኖስን (Julian the Apostate) በረቀቀ ጦር ወግቶታል።

❖ በደብረ ምጥማቅ እመቤታችን ትገለጥ በነበረ ጊዜ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከቅዱስ ቴዎድሮስ በመቀጠል ይመጣ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ነበር።

❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አርከ ሥሉስም የቅዱስ መርቆሬዎስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“ሰላም ለከ መርቆሬዎስ ዘሮም
መስተጽዕነ ፈረስ ጸሊም
አመ አንደዱ ታሕቴከ ውሉደ መርገም
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍሕም”

(በጥቊር ፈረስ ላይ የተቀመጥኽ የሮም ሰው ለኾንኸው ለመርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባኻል፤ የመርገም ልጆች ከሥርኽ እሳትን ባነደዱ ጊዜ ከተገረፈው ሰውነትኽ በብዙ ዝናብ አምሳል የፈሰሰው ደም ፍሙን አጠፋው) እያለ መስክሮለታል፡፡

❖ ሊቁም በአድናቆት በመሆን፦
“ሮማዊ ግሩም
በመንፈስ ቅዱስ ሕቱም
መዐዛ ቅዳሴከ ጥዑም ከመ ጽጌ ገዳም
ነዓ ነዓ ማዕከሌነ ቁም
በበዓልከ ትባርከነ ዮም”
(ግሩም ሮማዊ በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ፤ እንደ ምድረበዳ አበባ የምስጋናህ መዐዛ የጣፈጠ መርቆሬዎስ በበዓልህ ዛሬ ትባርከን ዘንድ ና ና በመካከላችንም ቁም) ይለዋል።

❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦

“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል
ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡
(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሶታል፨

[የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን፤ እናንተም በአስተያየት መስጫው ላይ በረከቱ እንዲያድርባችሁ ቅዱስ መርቆሬዎስን አወድሱት]


✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ታቦተ ጽዮን

✨እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ታቦተ ጽዮን የፊልስጥኤማውያን ጣዖት ዳጎንን ለሰባበረችበት (ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ 1ኛ ሳሙ 5)፣ ወደ ኢትዮጵያ ገብታ አክሱም ለመጀመርያ ጊዜ ለከበረችበትና ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት በተአምራት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ለተገኘችበት ለዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።

✍ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰላለች፤ ይህን ለመረዳት ስለ ታቦተ ጽዮን አሠራርና መንፈሳዊ ትርጉም አስቀድመን ልናውቅ ይገባናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ታቦተ ጽዮንን እንዲሠራ ብልሃትን፣ ጥበብን፣ ማስተዋልን፣ ዕውቀትን ይለይ ዘንድ መንፈሱን ያሳደረበትን ከይሁዳ ወገን የሆነውን ባስልኤልን መረጠ /ዘፀ.፳፭፥፱/፡፡ እርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ማስተዋል ከማይነቅዝ እንጨት ርዝመቷ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱዋ አንድ ክንድ ተኩል፤ ቁመቷ አንድ ክንድ ተኩል እንዲኖራት አድርጎ ታቦቷን ሠራት፡፡ በመቀጠል በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ ለበጣት፣ ከታቦቷም ዙሪያ የወርቅ አክሊልን አደረገላት፡፡ ካህናት ታቦተ ጽዮንን ለመሸከም እንዲረዳቸውም በአራቱም መዓዘናት በወርቅ የተሠሩ ቀለበቶችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገቡ ሁለት መሎጊያዎችን ሠራ፡፡ ከጥሩ ወርቅም የስርየት መክደኛውን በቃል ኪዳን ታቦቷ ላይ በርዝመቷና በወርደዋ ልክ ሠራ፡፡ የስርየት መክደኛውን እንዲጋርዱት አድርጎም ጥሩ ከሆነ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ኪሩቤልን ሥሎ በስርየት መክደኛው ግራና ቀኝ አስቀመጣቸው፡፡ እነዚህ በጥሩ ወርቅ የተሠሩት ሁለቱ ኪሩቤል ፊታቸው ወደ ስርየት መክደኛው ሆኖ እርስ በእርሳቸው እንዲተያዩ ተደርገው የተሠሩ ናቸው፡፡ በዚህ በስርየት መክደኛው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል እግዚአብሔር ለሙሴ እየተገለጠ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር በግልጽ ያነጋግረው ነበር፤ ለሕዝቡም በደመና ዐምድ ይታያቸው ነበር  /ዘፀ.፰፥፲፩፤ ፳፭፥፳፪-፴፫/፡፡

ወደ ምሥጢሩ ትርጓሜ ስንመለስም ታቦተ ጽዮን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ስትሆን፣ በውስጧ የያዘችው የሕጉ ጽላትም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቷ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቷ የእመቤታችንን ንጽህና የሚያመለክት ሲሆን፣ በውጪም በውስጥም በጥሩ ወርቅ መለበጧ ደግሞ ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል መሆኗን የሚያስረዳ ነው፡፡ ታቦተ ጽዮን በግራና በቀኝ በኩል በተዘጋጁ አራት ከወርቅ የተሠሩ ቀለበቶች ነበሯት፤ በእነዚያ የወርቅ ቀለበቶች ውስጥም ሁለት መሎጊያዎች ይገቡባቸው ነበር፡፡ ታቦቷን ለማንቀሳቀስ ባስፈለገ ጊዜ አራት ሌዋውያን ካህናት በመሎጊያዎቹ ይሸከሟታል፡፡ ይህ ሥርዐት በሰማያትም የሚታይ እውነታ ነው፡፡ የጌታን መንበር ገጸ ሰብእ፣ ገጸ ንሥር፣ ገጸ ላህምና ገጸ አንበሳ ያላቸው አርባዕቱ እንስሳት ይሸከሙታልና /ኢሳ.፮፥፩-፭፤ ሕዝ.፩፥፩-፲፮/፡፡ ለአማናዊቷ ታቦት ለቅድስት ድንግል ማርያምም ሰላምን የሚያወሩ፣ መልካም የምሥራችንም የሚናገሩ፣ መድኃኒትንም የሚያወሩ፣ ጽዮንንም;‹‹አምላክሽ ነግሦአል›› የሚሉ፣ እግሮቻቸው በተራሮች ላይ እጅግ ያማሩ የእርሷንና የጌታችንን ስም ተሸክመው ወንጌልን ለዓለም የሚሰብኩ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን አሏት /ኢሳ.፶፪፥፯/፡፡ የስርየት መክደኛው መቀመጫው የንጹሐን አንስት፣ መክደኛው የንጹሐን አበው፣ ግራና ቀኙ የሐናና የኢያቄም ምሳሌ ነው፡፡ በክንፎቻቸው የጋረዱት; ኪሩቤልም የጠባቂው መልአክ ቅዱስ ሚካኤልና የአብሣሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ምሳሌዎች ናቸው፡፡

የስርየት መክደኛው ስርየቱ የሚፈጸምበት ስፍራ ቢሆንም ነገር ግን በዚህ ቦታ ምንም ዓይነት መሥዋዕት አይቀርብም ነበር፡፡ ይህም በጊዜው አማናዊው መሥዋዕት ገና እንዳልተሠዋ ያስገነዝበናል፡፡ ይህ ስፍራ እግዚአብሔር ለሙሴ የሚገለጥበት ቦታ ነው፤ ከእርሱ ውጪ ሌላ ነገር በእዚያ ላይ ማረፍ አይችልም ነበር፡፡ ከዚህም የምናስተውለው አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን ሊፈጽም ሰው በሆነ ጊዜ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብበት ልዩ ስፍራ እንዳዘጋጀ ያመላክተናል፡፡ይህ ስፍራ አማናዊ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቦታ እንደሚያስፈልግ የሚያስገነዝብ ስፍራ ነው፡፡ ይህን ለማመልከትም ለኃጢአት ስርየት የቀረበው መሥዋዕት ከታረደ በኋላ ካህኑ ደሙን በጣቱ እየነከረ ሰባት ጊዜ በስርየት መክደኛው አንጻር በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ይረጨው ነበር /ዘሌ.፬፥፮/፡፡ነገር ግን ይህ ደም ከስርየት መክደኛው ላይ አያርፍም ነበር፤ ምክንያቱም በዚህ ስፍራ መቅረብ የሚገባው አማናዊው መሥዋዕት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነውና፡፡

ይህ የስርየት መክደኛ ለእኛ የሚያስተላለፈው ተጨማሪ መልእክትም አለው፡፡ይኸውም አማናዊው መሥዋዕት ክርስቶስ መሥዋዕት ሆኖ ዓለምን ማዳኑ እንደማይቀርና መሥዋዕቱ የሚቀርብበት ስፍራም በቅድስተ ቅዱሳኑ (ቤተ መቅደሱ) ውስጥ እግዚአብሔር በምሕረት በሚገለጥበት በቃሉ ማደሪያ በጽላቱ ላይ መሆን እንደሚገባው ያስገነዝበናል/ዕብ.፬፥፲፮/፡፡ ይህም እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ ሚልክያስ ላይ አድሮ ‹‹ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየስፍራውም ስለ ስሜ ዕጣንን ያጥናሉ፤ ንጹህም ቍርባን ያቀርባሉ፤›› /ሚል.፩፥፲፩/ በማለት እንደ ተናገረው የስርየት መክደኛው አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ቍርባንን ለምትፈጽምበት ጽላት ወይም ታቦት ምሳሌ መሆኑን ያሳየናል፡፡ የስርየት መክደኛውን የሚጋርዱት በጥሩ ወርቅ የተሠሩት የኪሩቤል ምስሎችም አማናዊው መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ በዙሪያው ረበው የሚገኙ የመላእክት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ሁለቱ ኪሩቤል የተባሉት ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡ ይህን ለማስገንዘብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመንበረ ታቦቱ ላይ ምስለ ፍቁር ወልዳ እንዲቀመጥ ታዝዛለች፡፡ ምስለ ፍቁር ወልዳን  ላስተዋለ ሰው በትክክል የታቦተ ጽዮንን መንፈሳዊ ትርጕም ይረዳል፡፡

ታቦተ ጽዮን ከሌሎች የብሉይ ኪዳን ንዋያተ ቅድሳት በተለየ መልኩ እጅግ ግሩም የሆነ ምሥጢርን በውስጧ ይዛለች፡፡ ይህን ድንቅ ምሥጢር ለመረዳትም አንድ ምሳሌ እንመልከት፤ ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑ ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ መዝሙርን አቅርቦ ነበር /፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፯/፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሚሆን ድርጊት በሐዲስ ኪዳንም ተፈጽሟል፡፡ ይኸውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅድስት ኤልሳቤጥ ሰላምታ በሰጠቻት ጊዜ የስድስት ወር ፅንስ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የእመቤታችንን የሰላምታ ድምፅ በመስማቱ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሆኖ በደስታ ዘሏል (ሰግዷል) /ሉቃ.፩፥፵፬/፡፡ ቅዱስ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እየተደሰተ ለአምላኩ የምስጋና ቅኔን መቀኘቱም ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳናችን ምክንያት የሆነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን በቃል ኪዳኗ ታቦት በኩል አስቀድሞ በዓይነ ሕሊና ስለ ተመለከታቸው ነበር፡፡

እንኳን አደረሰን። ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን። መልካም በዓል።

የኅዳር 21(ጽዮን ማርያም) በዓለ ንግሥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የት የት ይከበራል?

ህዳር 21

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በዓለ ንግሡ ይከበራል። 

1) ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ካቴድራል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አጠና ተራ

2)አውግስታ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ

3) ፍኖተሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ብርጭቆ ኮንዶሚንየም

4) ማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ የሺ ደበሌ

5) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦አዲስ ከተማ/ክ/ከ አውቶብስ ተራ

6) ኮተቤ  ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤልና ኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ መሳለሚያ

7) ደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል አደባባይ

8) ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  ካቴድራል

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጉርድ ሾላ

10) ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማያት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አባዶ

11) የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጎሮ

12) አንቆርጫ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አንቆርጫ

13) ቦሌ ኆህተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ገርጂ

14) መሪ ቅድስት ሥላሴ፤ቅዱስ ኡራኤል፤ቅድስት ድንግል ማርያም፤ቅዱስ  ጊዮርጊስ ወአቡነ አረጋዊ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ መሪ

15) ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም አብያተ ክርስትያናት

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ፈረንሳይ 41 ኢየሱስ

16) መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

ልዩ ስም፦አራዳ ክ/ከ አምስት ኪሎ

17) መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል፤ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ቅድስት አርሴማ  ገዳም

ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ

18) ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አራዳ ክ/ከ አርበኞች መንገድ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል

19) ቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም

20) ብሔረ ጽጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያምና መድኃኔዓለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ብሔረ ጽጌ

21) ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ታቦት ማደሪያ

22) ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ ልደታ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ

23) ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል ፍላወር

24) ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት ማርያም

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጀሞ 3 መስታወት ፋብሪካ ጀርባ

25) ሐመረወርቅ ቅድስት ማርያም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 5 ወርቁ ሰፈር

26) ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ለቡ(ፉሪ)
 
27) ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ ወ ገብረ ክርስቶስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ ወረዳ 1 ዘነበ ወርቅ

28) ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ፈጬ

30) ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ሰርጢ ማርያም

31) ቀርሳ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ልደታ ለማርያምና አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ቀርሳ

32) ቂሊንጦ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ድንግል ማርያም

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 9  ቂሊንጦ

33) መንበረ ልዑል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ ክርስቲያን

ልዩ ስም፡-ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላፍቶ 58 ማዞሪያ

34) ርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም  ቤ/ክ

ልዩ ስም፡-ጉለሌ /ክ/ከ እንጦጦ ማርያም

እናስተዋውቃችሁ – ጣና ቂርቆስ

ጣና ቂርቆስ በጣና ሀይቅ ውስጥ ከሚገኙት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት አንዱና ቀዳማዊዉ ሲሆን የተመሠረተው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ982 ዓ.ዓ ነው።

የንጉስ ሰለሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒልክ ከእሥራኤል ታቦተ ጽዮንን አጅበው በታቦተ ጽዮን መሪነት በፈቃደ እግዚአብሔር የመኳንንት ልጆችና ታቦተ ጽዮንን የሚያገለግሉ ካህናት እንዲሁም ከሌዋዉያን በጠቅላላ ብዙ ሺህ ህዝብ አስከትሎ ወደ ደሴቱ በመምጣት ይህንን ታላቅ ገዳም መሠረተው፡፡ የቦታውንም ስም ሳፍ ጽዮን መካነ ሣህል በማለት ሠይመውታል፡፡


እስራኤላውያን ካህናት ታቦተ ጽዮንን ከዚህ ገዳም ሲያስቀምጡ አብሮ የመጣውን ህዝብ ከባህር ውጭ ባለው ሥፍራ ሥላሰፈሩት እስከ ዛሬ ድረስ አካባቢው ነገደ እስራኤል በመባል ይታወቃል፡፡ ከመጡት እስራኤላውያን ካህናት መካከል የሊቀ ካህኑ የሣዶቅ ልጅ አዛርያስ ይገኝበታል፡፡ ካህኑ አዛርያስ አምልኮተ እግዚአብሔርንና መስዋዕተ ኦሪትን ካስፋፋ በኋላ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ በጣና ቂርቆስ ደሴት ነበር መካነ መቃብሩ ያረፈው፡፡ መካነ መቃብሩ የቃል ኪዳኑ ታቦት ድንኳን ካረፈበት ምስራቅ አቅጣጫ በሁለት የድንጋይ ቋጥኞች መካከል ይገኛል፡፡

የጣና ቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ከገዳሙ ከፍተኛ ቦታ ላይ የተሰራ ሆኖ የቃል ኪዳኑ ታቦት (ጽላተ ሙሴ) ካረፈችበት ቦታ ምዕራብ አቅጣጫ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የቤተ-ክርስቲያኑ ቅርጽ አራት ማዕዘን የሆነበት ምክንያት የቃል ኪዳኑ ታቦት ድንኳን አምሳያ እንደሆነ መነኮሳት ይገልፃሉ፡፡


ህገ ኦሪትና አዲስ ኪዳን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከበትና የጽላተ ሙሴ ማደሪያ የሆነው ሣፋ ጽዮን ደብረ ሣህል ወይም የዛሬዋ ጣና ቂርቆስ አንድነት ገዳም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት ዘመኗ አረጋዊ ዮሴፍንና ቅድስት ሶሎሜን አስከትላ በመልአኩ ዑራኤል መሪነት ከዚህ ታላቅ ገዳም 3ወር ከ10 ቀን ከልጇ ጋር ተቀምጣበታለች፡፡


እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ታላቅ ገዳም ሳለች ይመራ የነበረዉ መልዓክ ለዮሴፍ በህልሙ “ሄሮድስ ስለሞተ ህፃኑንና እናቱን ይዘህ ተመለስ” በማለት ሲነግረው ዮሴፍም ወደ ህፃኑ በመቅረብ /ፀአና በደመና/ በደመና ጫናት በማለቱ የገዳሙና የሀይቁ መጠሪያ ስም ጣና በመባል እደቀረ ይነገራል፡፡


የኢትዮጵያ ብርሀን ተብለው የሚጠሩት አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሀን ከነገሥታቱ ጋር ወደ እዚህ ቦታ በመምጣት የመጀመሪያውን የክርስትና እምነት ግዝረትን ሽረው ጥምቀትን፡ መሥዋዕተ ኦሪትን ሽረዉ አማናዊዉን የክርስቶስ ስጋና ደም በመሠዋት የክርስትና እምነትን አጽንተውበታል፡፡

አቡነ ሰላማ ጥምቀትን ብቻ ሳይሆን አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፀምበትን ታቦተ ህግ በቦታው አራት ጽላት በመቅረፅ በዛን ጊዜ እምነቱ ይስፋፋባቸው ወደ ነበሩት ሀገራት በትግራይ አክሱም ፅዮን፡ በጎጃም መርጦ ለማርያም እና ጣና ቂርቆስ፡ በወሎ ተድባበ ማርያምን በማስተከል ሁሉንም ታቦታት ታቦተ ፅዮን በማለት እንደሰየሟቸው በቦታው ያለው ታሪክ ያትታል፡፡


አቡነ አረጋዊና አፄ ገብረ መስቀል ወደዚህ ታላቅ ገዳም በመምጣት በረከትን አግኝተዎል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በገዳሙ ለአምስት አመታት በመቀመጥ ምልክት የሌለውን ድጓ ጽፎ ለገዳሙ አበርክቷል፡፡
ብዙ ቅዱሳን አባቶቻችንና ቅዱሳት አንስት እናቶቻችን በምነና እና በጸሎት ጸጋ እግዚአብሔር አግኝተውበታል።

የተለያዩ ነገሥታት አፄ የተባሉባቸውን ዘውዶች፡ አክሊሎች፡ የማዕረግ ልብሶች ጌጣጌጦች እንዲሁም ሌሎች የከበሩ ዕቃዎች እስከ ዛሬ ተጠብቀው የሚኖሩበት የሀይማኖት ማዕከልና የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ማሕደርና መሠረት ነው፡፡


ጣና በአጠቃላይ በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች ሲኖሩት 27 ገዳማትን አቅፎ ይዟል።ገዳማቶች በ14ኛ ምእት ዓመት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ባመነኮሷቸው ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ተብለው በሚጠሩት ቅዱሳን አባቶች የተመሠረቱ ናቸው።

ከገዳማቶች መካከል፦
ደብረ ማርያም
ክብራን ገብርኤል
ዑራ ኪዳነምሕረት
መሀል ዘጌ ጊዮርጊስ
አቡነ በትረ ማርያም
አዝዋ ማርያም
ዳጋ ኢስጢፋኖስ
ይጋንዳ ተክለሃይማኖት
ናርጋ ሥላሴ
ደብረ ሲና ማርያም
ማንድባ መድኃኔዓለም
ጣና ቂርቆስ
ክርስቶስ ሠምራ ገዳም
ራማ መድኃኔዓለም
ኮታ ማርያም…እና ሌሎችም ገዳማቶች ይገኙበታል።

ኅዳር 12- የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባሉ በየትኞቹ ገዳማትና አድባራት ይከበራል?

1) ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ

ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ዊንጌት ጠሮ አራት መንታ

2)የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም

ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ልኳንዳ ፈጥኖ ደራሸ ካምፕ

3)ማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ የሺ ደበሌ

4)በደብረ መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም ወቅድስት ልደት ወቅድስት አርሴማ ገዳም

ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ አስኮ ካኦጄጄ ዱቄት ፋብሪካ ከፍ ብሎ ቃሌ ተራራ ላይ ነው፡፡

5)ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦አዲስ ከተማ/ክ/ከ አውቶብስ ተራ

6)ቤተል ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ ቤተል

7)የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሾላ መገናኛ

8)ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ልደታ ክ/ከ ጎላ

9)ኮተቤ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሉቄ

10)ደብረሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል አደባባይ

11)ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማያት ወቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አባዶ

12)የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጎሮ

13)ቦሌ ኆህተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ገርጂ

14)ኮተቤ ደብረ ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ቅድስት ኪዳነምህረት እና አቡነ ሀብተማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ ካራ

15)ሲኤምሲ ደብረ ጽባህ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሲኤምሲ

16)አንቀፀ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ራስ ካሳ

17)መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ወቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ 6ኪሎ

18)ጉራራ ምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ፈረንሳይ ጉራራ

19)መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል፤ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ቅድስት አርሴማ ገዳም

ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ

20)ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አራዳ ክ/ከ አረበኞች መንገድ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል

21)ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጎፋ

22)አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦ቂርቆስ ክ/ከ አፍሪካ ኅብረት

23)ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ካቴድራል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ

24)ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ ልደታ

25)ፉሪ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጋራ ኦዳ

26)መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ
27)ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ላፍቶ

28)ሐመረወርቅ ቅድስት ማርያም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 5 ወርቁ ሰፈር

29)ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቤተል

30)ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ሰፈረ ገነት

31)ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ለቡ(ፉሪ)

32)አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ጋራው መድኃኔዓለም

33)ቃሊቲ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ ሰፈረ ገነት

34)ቂሊንጦ መካነፍስሐ ቅዱስ ሚካኤል እና በዓታ ለማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ ቂሊንጦ አደባባይ

35)ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ አቃቂ ኬላ ዝቅ ብሎ

36)ሣሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከሣሎ

37) ቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል እና ፃድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተክርስቲያን

ልዩ ስም:- ቦሌ ሚካኤል